የዚህ ራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ እንደመሆኔ ፣ የእኔ ስራዎች የሚያተኩሩት ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሰፊውን ደቡባዊ ዓለም የሚቀርጹ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ነው። በሂሳዊ ትንተና እና ጥልቀት ባላቸው ውይይቶች፣ የእነዚህኑ ቃጣናዎች የውጭ ፖሊሲ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የኢኮኖሚ አጋርነት እና የደህንነት ፈተናዎች እንዴት እንደሚመሩ በዝግጅቶቼ እዳስሳለሁ። የብዝኃ ኃያላን ዓለምን መነሻ በማድረግ ፣ ያልተወከሉ ድምጾችን በማጉላት እና አዳዲስ ዕይታዎችን ወደ ዓለም አቀፋዊ የውይይት መድረክ የማምጣት አላማ አለኝ ።