የግላዊነት ፖሊሲ

ይህ የግላዊነት ፖሊሲ በሩሲያ ፌዴሬሽን ድንጋጌዎች እና በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት፤ "በግል መረጃ ዙርያ" እ.አ.አ ሐምሌ 27፣ 2006 የወጣውን የሩሲያ ፌዴሬሽን ፌዴራላዊ ሕግ ቁጥር 152-FZ እና አጠቃላይ የመረጃ ጥበቃ ደንብ፤ በተለይም በተፈጥሮ ሰዎች ግላዊ መረጃ አጠቃቀም እና የዚህ መርጃ ነጻ ዝውውርን በተመለከተ እ.አ.አ ሐምሌ 27፣ 2016 ሥራ ላይ የዋለውን የአውሮፓ ፓርላማ እና የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 2016/679 እና የተሻርውን መመሪያ 95/46/EC (አጠቃላይ የመረጃ ጥበቃ ደንብ) ወይም ጂዲፒአር ጨምሮ ግን ሳይወሰን አካቶ የተቀረጸ ነው፡፡
በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ እና በሚመለከትው ሕግ መሠረት የእርስዎን መረጃ ለመጠበቅ አፋጣኝ እርምጃ እንወስዳለን እንዲሁም የእርስዎ የግል መረጃ ዓለም አቀፍ መስፈርትን በጠበቀ መልኩ ጥቅም ላይ እንደሚውል እና እንደሚጠበቅ ዋስትና እንሰጣለን፡፡
የእርስዎን ግላዊ መረጃ የምንጠቀምበትን አላማ ለመረዳት እና በኤጀንሲው ጥቅም ላይ የሚውለውን የግል መረጃ በተመለከት መብትዎትን ለማስከበር ይህን የግላዊነት ፖሊሲ በጥንቃቄ ያንብቡ፡፡
ይህን የግላዊነት ፖሊሲ በተቻለ መጠን ግልጽ እና ቀላል ለማድረግ ሞክረናል።
ይህ የግላዊነት ፖሊሲ በሩሲያኛ ቅጂ ጸድቆ አስፈላጊ ከሆነ ወደ ውጭ ቋንቋዎች ይተረጎማል።
የእርስዎን የግል መረጃ አጠቃቀም ሂደት ወይም ጥበቃን በተመለከተ ማንኛቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም ይህንን የግላዊነት ፖሊሲ ማሻሻል የሚቻልባቸው ማንኛቸውም ጥቆማዎች ወይም በይፋ የጸደቀውን ስሪት መከለስ ከፈለጉ እባክዎን በክፍል 13 "አድራሻ" ውስጥ ያለውን መረጃ በመጠቀም መልዕክት ይላኩልን።
1. የአጠቃቀም ወሰን
ይህ የግላዊነት ፖሊሲ የመረጃ ንብረቶቻችንን (ድረ-ገጽ፣ የሞባይል መተግበሪያ) ስትጠቀም እና ከመረጃ ሀብቶቻችን አጠቃቀም ጋር ያልተያያዙ ተግባራትን በምንፈጽምበት ጊዜ የእርስዎን ግላዊ መረጃ እንዴት እንደምንሰበስብ እና እንደምናስኬድ ለማሳወቅ የተነደፈ ነው።
ይህ የግላዊነት ፖሊሲ በክፍል 5 "የግላዊነት ማስታወቂያ" ውስጥ ለተገለጹት ሂደቶች ይሠራል::
የመረጃ ንብረቶቻችንን (ድረ-ገጽ፣ የሞባይል መተግበሪያ) ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ የሌሎች አገልግሎት አቅራቢዎች መረጃዎች እና ይህ የግላዊነት ፖሊሲ የሚይመለከታቸው ማስፈንጠሪዎች ሊይዙ እንደሚችሉ ይገንዘቡ፡፡
አጋሮቻችን የተጠቃሚ መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ እናስገድዳለን ስለሆነም እምነት ከምንጥልባቸ ኩባንያዎች ጋር ብቻ እንሠራለን፡፡
2. ጥቅም ላይ የሚወሉ የግለሰባዊ መረጃዎች ምድቦች
ከዘር፣ ከጎሳ፣ ከፖለቲካ አመለካከት፣ ከሃይማኖታዊ ወይም ፍልስፍና እምነት፣ ከጤና፣ ከወሲብ ሕይወት ወይም ከባይሎጂያዊ ባህሪያት ተያይዞ እርሶን ለመለየት አዳጋች የሆኑ ግላዊ መርጃዎቸን አንጠቀምም፡፡
ሚዲያውን በሚቆጣጠር ተገቢ ሕግ ካልተቀመጠ በስተቀር የግል መረጃዎትን ከሕዝብ ምንጮች አንሰበስብም፡፡
3. የግል መረጃ ተገዢዎች ምድቦች
የግል መርጃ ርዕሰ ጉዳዮች የኤጀንሲው ሠራተኞች፣ ተወካይ ቢሮዎቹን፣ቅርንጫፎች፣ ቢሮዎች፣ የኤጀንሲው ድረ-ገጽ ተጠቃሚዎች፣ የሞባይል መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች፣የኤጀንሲው አጋሮች፣ ደንበኞች፣ ተቋራጮች እና ተወካዮቻቸው፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪዎች (ግል ድረ-ገጻቸውን፣ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸውን ወይም የይዘት መድረኮቻችውን የሚያስተዋውቁ ግለሰቦች) የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች፣ በኤጀንሲው በተሰናዱ ዝግጅቶች ተሳታፊዎች እና ለመረጃ አጠቃቅም ዓላማዎች ሌሎች የግላዊ መረጃ ተገዢዎችን ያካትታል፡፡
የግላዊ መረጃ አጠቃቅም ዓላማዎች በክፍል 5 "የግላዊነት ማስታወቂያ"ውስጥ ተዘርዝረዋል፡፡
ኤጀንሲው የአዋቂ ግለሰቦችን የግል መረጃ ይጠቀማል፡፡
4. ለአካለ መጠን ያልደርሱ ተጠቃሚዎች የግል መረጃ መሰብሰብ
የእኛ የመረጃ ንብረቶች (ድረ-ገጽ፣ የሞባይል መተግበሪያ) ለአካለ መጠን ያልደርሰው ተጠቃሚ ቤተሰብ ወይም ሕጋዊ ሞግዚት ካልፈቀደ ወይም አግባብ ባለው ሕግ ካልተደነገገ በስተቀር ለአካለ መጠን ያልደርሱ ግለሰቦችን ግላዊ መረጃ አይጠቀሙም፡፡
አግባብ ባለው ህግ ካልተደነገገ በስተቀር ለአካለ መጠን ያልደርሰ ተጠቃሚ ከ18 ዓመት በታች የሆነ ግለሰብ ነው። ልጅዎ የግል መረጃውን/መረጃዋን እንደሰጠ/እንደሰጠች ካመኑ እባክዎን በክፍል 13 "አድራሻ" ውስጥ ያለውን መረጃ በመጠቀም ያሳውቁን።
5. የግላዊነት ማስታወቂያ
5.1. የግል መረጃዎን በመታወቂያ ማስኬድ
የኤጀንሲው የመረጃ ንብረቶች (ድረ-ገጽ፣ የሞባይል መተግበሪያ) ለሚከተሉት ዓላማዎች የግል መረጃዎን በመጠቀም ሊለይዎት ይችላሉ፦
5.1.1. በዜና ድረ-ገጽ ላይ የግል መለያ ባህሪያትን ስለመስጠት
የዜና ድረ-ገጽ የዜና ይዘትን ወይም የዜና ሪፖርቶችን በመሰብሰብ እና በመልቀቅ ላይ ያተኮረ የኤጀንሲው የኦንላይን ሚዲያ ነው።
ግላዊ መረጃን የመጠቀም ዓላማ
ተጠቃሚዎች ከዜና እና ከአስተያየቶች ጋር በተያያዘ በሚነሱ ውይይቶች የሚሳተፉበትን እድል መፍጠር
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
በድረ-ገጹ የግል አካውንት ለመክፈት ስም ወይም የተጠቃሚ ስም እና ኢ-ሜይል ያስፈልጋል፡፡
አካውንትዎን ከከፈቱ በኋላ ፎቶ፣ እድሜ፣ ጾታ፣ የትውልድ ቀን፣ የትውልድ ቦታ፣ ሀገር፣ የጎግል እና የአፕል መታወቂያዎን ጨምሮ ሌሎች መረጃዎችን መጨመር ይችላሉ፡፡ ሆኖም ይህ እንደፍላጎትዎ የሚሆን ነው፡፡
የጎግል፣ የአፕል እና የማህበራዊ ሚዲያ መታወቂያዎን የሚሰጡም ከሆነ ድረ-ገጹ በራሱ የራስዎንና የአያትዎን ስም፣ ፕሮፋይል ፎቶ፣ የትውልድ ቀን፣ ጾታ፣ ኢ-ሜይል እና የምዝገባ ሁኔታ ጨምሮ በማህበራዊ ሚዲያ አካውንትዎ የሚገኙ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች መዘግቦ ይይዛል፡፡
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
የእርስዎ ስምምነት
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያው ጊዜ
አካውንትዎን እስከሚያጠፉ ወይም ስምምነትዎን ሲያቋረጡ (ወይም መረጃዎን እንድንሰርዝ እስኪጠይቁ)
ስምምነቱ የሚቋረጠው በአንቀጽ 8.7 በተቀመጠው "ስምምነት የማቋረጥ መብት" መሰረት ነው፡፡
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
በግል አካውንትዎ በኩል የጎግል፣ የአፕል እና የማህበራዊ ሚዲያ መታወቂያዎን ሲሰጡ መረጃዎ ወደ ሶስተኛ ወገኖች በዋናነትም ወደ ፌስቡክ ኢንክ. (ፌስቡክ)፣ ወደ ጎግል ኤልኤልሲ (ፋየርቤዝ፣ ጎግል አናሊሲስ)፣ ትዊተር ኢንክ. (ትዊተር)፣ ቭኮንታክቴ ኤልኤልሲ (ቭኮንታክቴ) እና አፕል ኢንክ. ሊተላለፍ ይችላል፡፡
ሆኖም የማህበራዊ ሚዲያ መታወቂያዎን በግል አካውንትዎ በኩል ካልሰጡ ወደ ሶስተኛ ወገኖች የሚተላለፍ መረጃ አይኖርም፡፡
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለማስተላለፍ
የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎን በግል አካውንትዎ በኩል ከሰጡ፤ የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በተሰማሩባቸው ሀገራት ግልጋሎት ላይ ሊውል ይችላል፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎን በግል አካውንትዎ በኩል ካልሰጡ ግን የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ብቻ ግልጋሎት ላይ ሊውል ይችላል፡፡
5.1.2 በሚዲያ ድረ-ገፅ በኩል ስለሚሰጡ የግል አካውንቶች
የሚዲያ ድረ-ገፅ ለቀጣይ አገልግሎትና ስርጭት እንዲውሉ በማሰብ የተፈጠሩ ፎቶ፣ ቪዲዮ፣ ኦዲዮ እና መሰል የዲጂታል መረጃ ውጤቶችን የያዘ የኤጀንሲ የመረጃ ምንጭ ነው።
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
የፎቶ ምስሎች፣ የግራፊክስ፣ የኢንፎግራፊክስ እና የኦዲዮቪዥዋል ይዘቶችን ለመጠቀም ፈቃድ መስጠት።
ለዚህ ዓላማ የሚውሉ ግላዊ መረጃዎች
የራስና የአባት (አያት) ስም፣ ኢ -ሜይል፣ መግቢያ፣ የኩባንያ ስም፣ የኩባኛው የሥራ አካባቢ፣ ከተማ፣ ሀገር፣ የቅጥር ቦታ፣ ሥራው መደብ፣ የፖስታ መረጃ ጠቋሚ፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር
ግላዊ መረጃዎትን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
ውል (የፈቃድ ስምምነት)
የግል መረጃዎን የማከማቻ ጊዜ
ውሉ (የፈቃድ ስምምነቱ) እስኪያበቃ
ውሉ ሲያበቃ ወደ ውስጥ ማህደራችን ይተላለፋል። ውሉ የሚመለከተው ሕግ በሚጠይቀው መሠረት በውስጥ ፋይል መመዝገቢያ ደንቦች የጊዜ ውሳኔ መሰረት ተከማችቶ ይቆያል፡፡
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
ግላዊ መረጃ ወደ ሶስተኛ ወገኖች አይተላልፍም
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለማስተላለፍ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ብቻ ግልጋሎት ላይ ይውላል
5.1.3. በንግድ መረጃ ድረ-ገጽ ላይ የግል መለያን ለድርጅቶች መስጠትን በተመለከተ
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
የንግድ አገልግሎቶችን ለመስጠት
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
ለኢ-ሜይል አድራሻ፣ ለኩባንያ ስም፣ ለመግቢያ እና ለዜና አቅርቦት ምዝገባዎች መረጃ አያያዝ
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
ውል (የፍቃድ ስምምነት)
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
ውሉ (የፍቃድ ስምምነት) እስኪያበቃ
ውሉ ሲያበቃ ወደ ውስጥ ማህደራችን ይተላለፋል። ውሉ የሚመለከተው ሕግ በሚጠይቀው መሠረት በውስጥ ፋይል መመዝገቢያ ደንቦች የጊዜ ውሳኔ መሰረት ተከማችቶ ይቆያል፡፡
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገን ስለማስተላለፍ
ግላዊ መረጃ ወደ ሶስተኛ ወገኖች አይተላልፍም
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ አገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ብቻ ግልጋሎት ላይ ይውላል
5.1.4. ውድድሮችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ማዘጋጅት
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
ለገበያ አላማ ውድድሮችን ወይም ዘመቻዎችን ለማዘጋጀት።
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
የማህበራዊ ሚዲያ መለያ፣ የመጀመሪያ ስም፣ የአያት ስም፣ የአባት ስም፣ ዕድሜ፣ ሀገር፣ የመልእክት መተግበሪያዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች፣ ስልክ ቁጥሮች፣ ኢ-ሜይል፣ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች፡፡
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
በውድድር ወይም በሌላ ሁነቶች ለመሳትፍ የተቀመጡ ደንቦች
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያው ጊዜ
እስከ ዝግጅቱ መጨረሻ ድረስ
የአሸናፊዎች መረጃ ሽልማታቸውን እስኪቀበሉ ድረስ ግልጋሎት ላይ ሊውል ይችላል
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
ሶስተኛ ወገኖች (አጋሮች፣ የሶስተኛ ወገን መድረኮች) ዝግጅቱን በማዘጋጀት ወይም ሽልማቶችን በማቅረብ (በፖስታ አገልግሎት ወይም በማጓጓዝ ወይም በአጋርነት) ከተሳተፉ የግል መረጃዎ ወደ እነዚህ ሶስተኛ ወገኖች ይተላለፋል።
ሶስተኛ ወገኖች ለአሸናፊዎች ሽልማት መስጠትን ጨምሮ የትኛውንም የውድድር መድረክ በማዘጋጀት ካልተሳተፉ፤ ኤጀንሲው ምንም አይነት የግል መረጃን ለሶስተኛ ወገኖች አያስተላልፍም።
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
ሶስተኛ ወገኖች (አጋሮች፣ የሶስተኛ ወገን መድረኮች) አንድ ሁነት በማዘጋጀት ወይም ሽልማትን (በፖስታ አገልግሎት፣ በማጓጓዝ አገልግሎት ወይም በእኛ አጋሮች) በማቅረብ ከተሳተፉ የእርስዎ የግል መረጃ በሩሲያ ፌዴሬሽን እና እነዚህ ሶስተኛ ወገኖች በሚንቀሳቀሱባቸው ሌሎች ሀገሮች ውስጥ ግልጋሎት ላይ ይውላል፡፡
ምንም ዓይነት ሶስተኛ ወገን ካልተሳተፈ የግል መረጃዎ ጥቅም ላይ የሚውለው በሩሲያ ፌዴሬሽን ውስጥ ብቻ ይሆናል፡፡
5.1.5. የኢሜል የዜና ኒውስሌተሮችን እና ማሳወቂያዎችን መላክ በተመለከተ
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
የዜና ኒውስሌተሮችን ለማሰራጨት
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
የመጀመሪያ ስም፣ የአያት ስም ፣ ኢ-ሜይል፣ አካባቢዎ (አድራሻ)፣ የኢ-ሜይል ደንበኛዎ
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
የእርስዎ ፈቃድ
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
ፈቃድዎን እስኪያቋርጡ ድረስ
ስምምነቱን የማቋርጥ ሂደት በአንቀጽ 8.7 "ፍቃድን የመሰርዝ መብት" ውስጥ ተገልጿል፡፡
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
የሮኬት ሳይንስ ቡድን (ሜይሊቺምፕ)፤ ሴንድፐልስ ኢንክ (ሴንድፐልስ) ይላካል፡፡
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን፣ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በጀርመን እና በሊትዌኒያ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል።
5.1.6. ግብረ መልስ መቀበል እና መስጠት
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
ከግለሰቦች ወይም ከድርጅቶች ተወካዮች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን (ቅሬታ እና ጥቆማዎችን) ተቀብሎ ለማደራጀት።
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
የመጀመሪያ ስም፣ የአባት ስም፣ የሥራ ቦታ እና የሥራ መደብ፣ አድራሻ፣ ሀገር፣ ስልክ ቁጥሮች እና ኢ-ሜይል
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
ችግርዎን ለመፍታት ግብረመልስ ማግኘትዎን ለማረጋገጥ
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
ችግርዎ እስኪፈታ ድረስ
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
የግል መረጃዎ ወደ ሶስተኛ ወገን አይተላለፍም
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ብቻ ግልጋሎት ላይ ይውላል
5.2. ያለእርስዎ መታወቂያ የግል መረጃዎን ስለመጠቀም
ድረ-ገጾችን እርስዎን እንደ ግለሰብ ሳይለይ መረጃዎችን ለሚከተሉት ዓላማዎች ይስብስባል
5.2.1. የመረጃ ምንጮችን (ድረ-ገጾች እና የሞባይል መተግበሪያዎች) ባህርይ በውስጣዊ የመተንተኛ ስርአቶች መተንተን
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
የድረ-ገጹን/መተግበሪያውን አሰራር ለማሻሻል፣ ይዘትን ለማቅረብ፣ በጣም ተዛማጅነት ያላቸውን የዜና ዘገባዎች ለማሳየት እና በኤጀንሲው ድረ-ገጽ/ሞባይል መተግበሪያ አማካይነት ደንበኞችን ታሳቢ ያደረጉ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት።
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
ኩኪዎች፣ የአይፒ አድራሻዎች፣ ቦታዎች፣ የሚጠቀሙትን የመሳሪያ አይነት እና የአስራር ስርዓት፣ የአሳሽ አይነት እና ስሪት፣ የመሳሪያ አይነት እና የስክሪን የጥራት ደረጃ፣ የትራፊክ ምንጭ (ድረ-ገጽ ወይም ማስታወቂያ) እና የስርዓተ ክወናው ቋንቋ እና ማሰሻ (ብራውዘር)፣የተጠቃሚው የኦንላይን እንቅስቃሴ
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
ሕጋዊ ፍላጎት
የእርስዎ መረጃ ስንጠቀም በዚህ ጉዳይ ላይ ሌላ ምንም አይነት ምክንያት ስለማይኖር በሕጋዊ ፍላጎትታችን ላይ ተመስርትን እንሰራልን። አፈጻጸማችን የሚወሰነው ቀለል ባለ መንገድ በምንሰጥዎ መረጃና ፍላጎትዎ ነው፡፡
የድረ-ገጻችን ተጠቃሚ ባህሪ ትንተና ሥራችን በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን እንዲያውቁ እንጠብቃለን፡፡ የተጠቀሰውን ግብ ለማሳካት የምናደርገው ማንኛውም የመረጃ ትንተና በመብትዎ እና በነጻነትዎ ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ እንደማይኖረው እናረጋግጣለን።
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
የማከማቻ ጊዜው እንደ ኩኪው አይነት ይወሰናል
ስለ ኩኪ አይነቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎን ነጻ የሶስተኛ ወገን ድረ-ገጾችን ይመልከቱ፡- ለምሳሌ፡ https://www.hotcleaner.com/cookie-editor/
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
የግል መረጃዎ ወደ ሶስተኛ ወገን አይተላለፍም
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ብቻ ግልጋሎት ላይ ይውላል
5.2.2የሶስተኛ ወገኖች የመረጃ ምንጮች ባህሪን (ድረ-ገጾች እና የሞባይል መተግበሪያዎች) መተንተን
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
የድረ-ገጹን/መተግበሪያውን አሰራር ለማሻሻል፣ ይዘትን ለማቅረብ፣ በጣም ተዛማጅነት ያላቸውን የዜና ዘገባዎች ለማሳየት እና በኤጀንሲው ድረ-ገጽ/ሞባይል መተግበሪያ አማካይነት ደንበኞችን ታሳቢ ያደረጉ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት።
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
ኩኪዎች፣ የአይፒ አድራሻዎች፣ ቦታዎች፣ የሚጠቀሙትን የመሳሪያ አይነት እና የአስራር ስርዓት፣ የአሳሽ አይነት እና ስሪት፣ የመሳሪያ አይነት እና የስክሪን የጥራት ደረጃ፣ የትራፊክ ምንጭ (ድረ-ገጽ ወይም ማስታወቂያ) እና የስርዓተ ክወናው ቋንቋ እና ማሰሻ (ብራውዘር)፣የተጠቃሚው የኦንላይን እንቅስቃሴ
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
የእርስዎ ፈቃድ
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
የማከማቻ ጊዜው እንደ ኩኪው አይነት ይወሰናል
1) ስለ ኩኪ አይነቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎን ነጻ የሶስተኛ ወገን ድረ-ገጾችን ይመልከቱ፡- ለምሳሌ፡ https://www.hotcleaner.com/cookie-editor/
2) ፈቃድዎን እስኪያነሱ ድረስ (መረጃው ጥቅም ላይ እንዳይውል መከልከል ይችላሉ)
ስምምነቱን የማቋርጥ ሂደት በአንቀጽ 8.7 "ፍቃድን የመሰርዝ መብት"ውስጥ ተገልጿል፡፡
ግላዊ መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
ይህንን ዓላማ ለማሳካት ከሶስተኛ ወገን አገልግሎቶች የመረጃ ምንጮች ጋር ግኑኝነት እንፈጥራለን፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች ለትንተና የእርስዎን ግላዊ መረጃ እንዲሰበስቡ እድሉን እንሰጣለን። በዚህ ገዜ የእርስዎ የግል መረጃ አጠቃቀም በእነዚህ የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶች የግላዊነት ፖሊሲዎች ተገዢ ይሆናል።
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ አገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የእርስዎ የግል መረጃ በሩሲያ ፌዴሬሽን፣ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በግብፅ እና በሚመለከታቸው የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶች በሚሰሩባቸው ሌሎች ሀገሮች ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል።
5.3. የመረጃ ምንጮችን ሳይጠቀሙ ለውስጣዊ ኤጀንሲ ዓላማዎች መረጃውን መጠቀም
ለሚከተሉት ዓላማዎች የመረጃ ምንጮችን ሳንጠቀም የእርስዎን የግል መረጃ ልንጠቀም እንችላለን
5.3.1. የኤጀንሲው ዝግጅት ወይም በኤጀንሲው ለተዘጋጀ ዝግጅት ለሚዲያ ተወካዮች ወይም ጦማሪዎች ማረጋገጫ ለመስጠት
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
የኤጀንሲው ዝግጅት ወይም በኤጀንሲው ለተዘጋጀ ዝግጅት የሚዲያ ተወካዮች ወይም ጦማሪዎች ማረጋገጫ ለመስጠት።
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
የመጀመሪያ ስም፣ የአያት ስም፣ የአባት ስም፣ ጾታ፣ ዜግነት፣ የመታወቂያ ሰነድ መረጃ፣ ፎቶግራፍ፣ የፓስፖርት ገጾች ቅጂ፣ የሥራ ቦታ እና የሥራ መደብ፣ የቪዛ ምድብ እና ቁጥር፣ ኢ-ሜይል፣ የእውቂያ ስልክ ቁጥሮች፣ ሀገሪቱን ለመጎብኘት ዓላማ።
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
የእርስዎ ፈቃድ።
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
ለማረጋገጫው ጊዜ እንዲሁም ከማረጋገጫ አንድ ዓመት በኋላ፡፡
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
በኤጀንሲው ዝግጅቱ ውስጥ ከተካተተ የግል መረጃዎ ለሶስተኛ ወገኖች ይተላለፋል።
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ አገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ውስጥ እና ዝግጀቱ በሚካሄድበት ሀገር ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
5.3.2. ለኤጀንሲው ዝግጅት ግብዣ
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
ለኤጀንሲው ዝግጅት፡፡
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
የመጀመሪያ ስም፣ የአያት ስም፣ የአባት ስም፣ ፎቶግራፍ፣ የሥራ ቦታ እና የሥራ መደብ፣ ኢ-ሜይል፣ ስልክ ቁጥሮች፣ የትምህርት ዲግሪ፣ ፕሮፋይል፣ የመልክት መተግበሪያ እና የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ።
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
የእርስዎ ፈቃድ።
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
እስከ ዝግጅቱ መጨረሻ፡፡
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
በኤጀንሲው ዝግጅቱ ውስጥ ከተካተተ የግል መረጃዎ ለሶስተኛ ወገኖች ይተላለፋል።
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ውስጥ እና ዝግጀቱ በሚካሄድበት ሀገር ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
5.3.3. የኤጀንሲውን አጋሮች፣ ኮንትራክተሮች እና ደንበኞች ተወካዮችን መረጃን ስለመጠቀም
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
የሲቪል ውልን መፈጸም፣ ማከናወን እና ማቋረጥ፤ ከኮንትራክተሩ ጋር ውል ማጽደቅ፡፡
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
የመጀመሪያ ስም፣ የአያት ስም፣ የአባት ስም፣ የሥራ ቦታ እና የሥራ መደብ፣ ኢ-ሜይል፣ ስልክ ቁጥር፡፡
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
ውልን (ማንኛውም ዓይነት ውል) ለመፈጸም እንዲሁም ለማከናወን የሚወሰዱ እርምጃዎች።
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
ውሉ እስኪፈጸም ወይም ውሉ እስኪቋረጥ/ እስኪያበቃ ድረስ፡፡
ውሉ እስኪቋረጥ/ እስኪያበቃ ኮንትራቱ ወደ ማህደሩ ይተላለፋል፡፡ ውሉ የሚመለከተው ሕግ በሚጠይቀው መሠረት በውስጥ ፋይል መመዝገቢያ ደንቦች የጊዜ ውሳኔ መሰረት ተከማችቶ ይቆያል፡፡
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
የግል መረጃዎ ወደ ሶስተኛ ወገኖች አይተላለፍም፡፡
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ብቻ ግልጋሎት ላይ ይውላል
5.3.4. የመገናኛ ብዙሃን የይዘት ውጤት
የግል መረጃን የመጠቀም ዓላማ
ለመገናኛ ብዙሃን ሥራዎች፡፡
ለዚህ ዓላማ የሚፈለገው ግላዊ መረጃ
የመጀመሪያ ስም፣ የአያት ስም፣ የአባት ስም፣ ፎቶግራፍ፣ የሥራ ቦታ እና የሥራ መደብ፣ ኢ-ሜይል፣ ስልክ ቁጥሮች፣ የትምህርት ዲግሪ፣ ፕሮፋይል፣ የመልክት መተግበሪያ እና የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ።
ግላዊ መረጃን ለመጠቀም ሕጋዊ መሰረቶች
ሕጋዊ ጥቅም
የእርስዎ መረጃ ስንጠቀም በዚህ ጉዳይ ላይ ሌላ ምንም አይነት ምክንያት ስለማይኖር በሕጋዊ ፍላጎትታችን ላይ ተመስርትን እንሰራልን። ሥራችን በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላሉ ክስተቶች ፈጣን ምላሽ መስጠት እና በዜና ይዘት መልክ ማቅረብን ያካትታል። እንደ መገናኛ ብዙሃን የዜና ይዘት በምንሠራበት ወቅት የግለሰብን መብቶች እና ነጻነቶች እስካልጣሱ ድረስ እነዚህ ግላዊ መረጃዎች ለህዝብ ክፍት ይሆናሉ፡፡ ይህንን እንዲያውቁ እንጠብቃለን።
ግላዊ መረጃን አከማችቶ የመጠቀሚያ ጊዜ
እንደ መገናኛ ብዙኃን የጋዜጠኝነት ተግባራችን ላልተወሰነ ጊዜ
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ወገኖች ስለማስተላለፍ
የግል መረጃዎ ወደ ሶስተኛ ወገኖች አይተላለፍም፡፡
የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማስተላለፍን በተመለከተ
የግል መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ብቻ ግልጋሎት ላይ ይውላል፡፡
5.3.5. ለመገናኛ ብዙሃን ወኪሎች የሚላኩ የዜና ጽሑፎች
የግል መረጃ አሰራር አስፈላጊነት
የዜና ጽሑፎችን ማሰራጨት
ለዚህ ዓላማ ጥቅም ላይ የሚውሉ ግላዊ መረጃዎች
የመጠሪያ ስም፣ የአያት ስም፣ የአባት ስም ፣የሥራ ቦታ፣ ስልክ ቁጥር ፣ ኢሜይል፣ ሃገር
ግላዊ መረጃዎች ጥቅም ላይ ለማዋል ህጋዊ መሰረቶች
የእርሶ ፍቃድ
የእርሶ ግላዊ መረጃ የሚከማችበት ጊዜ
የእርሶን ፍቃድ እስከሚሰርዙ ወይም እስከሚያነሱ ድረስ
የስምምነት አሰራር ፈቃድዎን ለማቆም በቁጥር 8.7 "ስምምነት ፈቃድ የማስቆም መብት" ተገልጿል።
ግላዊ መረጃዎችን ለሶሰትኛ ወገን አሳልፎ መስጠት
የግል መረጃዎች ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፈው አይሰጡም።
ግላዊ መረጃዎችን ለሶስተኛ ሀገር ወይም ለዓለም አቀፍ ተቋም መስጠት
ግላዊ መረጃዎ በሩሲያ ፌዴሬሽን ውስጥ ብቻ ይሰራል.
6. አውቶሜትድ የግለ ውሳኔ አሰጣጥ እና ምርመራ
ግላዊ መረጃዎ በሂደት ላይ በሚሆንበት ጊዜ አውቶሜትድ የግለ ውሳኔ አሰጣጥ እንዲሁም ምርመራ (ፕሮፋይሊንግ) አንጠቀምም።
7. የግል መረጃዎችን ማጥፋት
የግል መረጃዎች የሚያስፍለገውን ሂድት ካልፉ በኋላ ፣ የማከማቻ ጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ፣ ጉዳዩ በተግባር ላይ ባለው ሕግ ካልታወቀ ፣ ፈቃድ ስጪው አካል ፈቃዱን ካነሳ ወይም ከሰርዘ በኋላ የግል መረጃዎች ይጠፋሉ። የግል መረጃዎችም በህገ ወጥ መንገድ እንደተሰራ ከተረጋገጠ እንዲጠፉ ይዳረጋሉ።
8. መብቶች
8.1 ግላዊ መረጃዎን የማግኘት መብት
ግላዊ መረጃዎ አገልገሎት ላይ የሚዉልበትን ሂደት ፣ የሂደቱ አስፈላጊነት ወይም አሰራር ፣ ምድቦች ፣ ተቀባዮች ወይም ምድቦች, ከሌሎች አገሮች ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጨምሮ ፣ የማከማቻ ጊዜ, የእርስዎን መረጃዎችን የማቋረጥ ሁኔታዎች እና የግል መረጃዎን ምንጭ ከእኛ የማግኘት መብት አለዎት፡፡
በኤሌክትሮኒክ ፎርም መልኩ ያዘጋጀነውንና በመረጃ ቋታችን ዉስጥ ያለውን የእርስዎን መረጃዎች በግልጽ ተግባራዊ ድጋፍ የተሰጠው እንደሆን የግል መረጃዎን የኤሌክትሮኒክ ቅጂ የመጠየቅ መብት አለዎት።
8.2 ግላዊ መረጃዎን የማስተካከል መብት
ግላዊ መረጃዎ ትክልል ያልሆን፣ ያልተሟላ ወይም ጊዜው ያለፈበት ከሆን በእኛ በኩል ያለመዘግየት አእንዲታረም የማድረግ መብት አለዎት፡፡ አእንደአስፈላጊነቱ ራስዎ ሊያስተካክሉት ፣ ለምሳሌ የግል አካውንትዎን ሴቲንግ ወይም መቼት ውስጥ ፣ የግል መረጃዎን እንደተስተካከለም እናሳውቅዎታለን፡፡
8.3. የግል መረጃዎን የመሰረዝ መብት
የግል መረጃዎን በኛ በኩል በቶሎ እንድንሰርዘው ወይም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ እራስዎ እንዲያጠፉት የመጠየቅ መብት አለዎት። ለምሳሌ በግል አካውንትዎ ሴቲንግ ወይም መቼት ውስጥ ፡፡
የግል መረጃዎን መሰረዝ ወይም ማጥፋት ካልቻልን ፣ የአካውንቱ ባለቤት እንዳይለይና በግል መረጃዎ ስም እንዳይገለጽ እናደርጋለን ።
የግል መረጃዎን ካጠፋን ወይም ስም አእንዳይገለጽ ማድረጋችንንም እንዲያዉቁት እናደርጋለን።
8.4. የመገደብ (block) የማድረግ መብት
የግል መረጃዎን ጥቅም ላይ የማዋል ሂድት እንዲገደብ (block) እንዲደረግ የመጠየቅ መብት አለዎት፡፡ይህንን መብት መጠቅም የሚችሉትም በሚከተሉት ጉዳዮች ብቻ ነው ፡፡
1) የሰጡንን መረጃ ለማረጋገጥ በሰጡን በቂ ጊዜ ወስጥ የግል መረጃዎን ትክክለኛነት የሚያጠራጥር ነገር ከገጠዎት ፣
2) የግል መረጃዎች አጠቃቀም ከህግ አግባብ ውጪ ከሆነ እና የግል መረጃዎ አጠቃቀም መሰረዝን የሚቃወሙ ከሆነ
3) የግል መርጃዎን መጠቀም ባያስፈልገንም ፣ ህጋዊነትን እንዲይዙ ፣ እንዲከተሉ እንዲጠብቁ ማድረግ ሲያስፈልግዎ
4) የግል መርጃዎን መጠቀምን በተመልተ በአእኛ በኩል ሕጋዊት ምክንያት እስካልቀረበ ድረስ ሂደቱን መቃወም ይችላሉ
የግል መረጃዎን አሰራር ከተገደበ (ከተዘጋ)፣ እገዳው እስኪነሳ ድረስ ሂደቱን እናቋርጣለን ነገር ግን የግል መረጃዎን ማከማቸት እንቀጥላለን።
በክፍል 13 ላይ ‘‘ያግኙን’’ ያግኙን የተገለፀውን ዘዴ በመጠቀም ጥያቄ በመላክ በማንኛውም ጊዜ የግል መረጃዎን ከማዘጋጀት ከማገድ (block) ማስነሳት ይችላሉ፡፡
8.5. መረጃ የማንቀሳቀስ መብት
የግል መረጃዎን በተደራጀና ኮምፒዩተር-ማንበብ በሚቻል መልኩ የማግኘት እንዲሁም ይህንን መረጃ ወደ ሌላ ድርጅት የማዛወር መብት አለዎት።
መረጃህ በአንተ ፈቃድ ወይም በተፈረመበት ስምምነት ላይ ተመሥርቶ ወይም ይህ መብት ተግባራዊ በሆነ ሕግ በግልጽ ሲሰጥና በቴክኒክ ረገድ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ከሆነ ይህን መብት ልጠቀምበት ትችላለህ ።
8.6. የመቃወም መብት
መረጃዎን በሲስተም ሂደት ላይ ባለበት በማንኛውም ጊዜ በማስረጃ ላይ ተመስርተው ሂድቱን የመቃወም ላይ መብት አለዎት።
1) ለህዝብ ጥቅም የሚጠቅሙ ስራዎችን ማከናወን ወይም የተሰጠን ይፋዊ ስልጣን ለመጠቀም፤
2) በእኛ ወይም ሶስተኛ ወገን በሚከተላቸው ህጋዊ ፍላጎቶች ላይ በመመስረት እነዚህን ፍላጎቶች መከተል መብትህንና ነፃነትህን ለመጠበቅ አስፈላጊ ካልሆኑ
የግል መረጃዎቻችሁን ለመጠቀም የሚያስችል አሳማኝ ሕጋዊ ምክንያት ማሳየት ካልቻልን የግል መረጃዎቹን ለመጠቀም በሂደት ውስጥ እንዲያልፉ አናድርግም ።
በማንኛውም ጊዜ የግል መረጃዎን ለገበያ ማቅረብን ፣ ማንነትን ለመበየን ጨምሮ፣ በሥራ ላይ ባለው ሕግ በግልጽ የተደነገገ ከሆነ እንዲህ ዓይነቱ ተግባር መቃወም ይችላሉ፡፡
8.7. ስምምነትን የማቋረጥ መብት
የግል መረጃዎ በእርስዎ ፈቃድ የሚሰራ ከሆነ, ስምምንቱን የማቋረጥ መብት አለዎት፡፡ ቀላል የሆነ 'የስምምነት ማቆም' አሰራር እንጠቀማለን።
1) በኢሜይል የሚላኩ የዜና ጽሑፎች ስምምነት ማቋረጥ
ከዚህ በታች ያለውን ማንኛውም ዘዴ በመጠቀም ስምምነቱን ማቋረጥ ይችላሉ
ሀ) ወደኢሜይል የሚገቡ መልዕክቶችን ለማስቆም ‘‘አንሰብስክራይብ’’ ወይም "unsubscribe" የሚለውን አማራጭ ይንኩ
ለ) ለኢሜይል የዜና ጽሑፎች ለማቆም የስምምነት ማሳውቂያ መልዕክት ይላኩልን
ሐ) በግል አካውንት ሴቲንግ ውስጥ የኢሜይል የዜና ጽሑፎች ማሳወቂያውን ያጥፉ
2) በድረ-ገፁ ላይ ባለ የግል አካውንትዎ አማካኝነት ከስምምነት መውጣት
ከዚህ በታች ያለውን ማንኛውም ዘዴ በመጠቀም ስምምነቱን ማቋረጥ ይችላሉ
ሀ) በድረ-ገፆች ላይ ያለውን የእርስዎን አካውንት በግላዊ አካውንት ሴቲንግ ውስጥ በመግባት የግል አካውንትዎን ይሰርዙ (በግል አካውንትዎ ሰርዝ የሚል ማስፈንጠሪያን ያገኛሉ)
ለ)በክፍል 13 ወሰጥ ባለው ‘‘ያግኙን’’ አድራሻ ስምምነት ማቋረጥዎን ማሳውቂያ መልዕክት ይላኩልን፡፡
3) የኩኪ አሰራር (የቀነሰ የኩኪ አሰራር) ስምምነት ማውጣት ፤ በድህረ ገፅ ላይ ባለው
የግል መረጃ መከታተያ ሴቲንግ መሰረት ወይም የኩኪ ወይም አዉቶማቲክ ሎጊንግ ፖሊሲን በመጠቀም ከስምምነቱ መውጣት ይችላሉ ( ሂደቱን መሰረዝ) ይችላሉ፡፡
በሚጠቀሙት የኢንተርኔት መገልገያ መሳሪያ ላይ አንድ ጊዜ የኢንተርኔት መቃኛ ከመረጡ በኃላ እንደ ኩኪ ሰነዱ አይነት በራሱ/ አዉቶማቲካሊ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
በራሱ/ አዉቶማቲካሊ መሰረዝ ተግባራዊ ካልሆን ሂደቱ የእርሶ ከስምምነቱ ራስዎን ማውጣትን መሰረት በማድረግ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
4) ከመረጃ ሀብቶቻችን አጠቃቀም ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የግል መረጃዎችን
የማሰባሰብ ስምምነት መውጣት ይችላሉ ፡፡ በክፍል 13 ላይ "ያግኙን" የተገለፀውን ዘዴ በመጠቀምና ማሳውቂያ በመላክ ፈቃድዎን መሰረዝ ይችላሉ፡፡
8.8. ለተቆጣጣሪ ባለስልጣን ቅሬታ የማቅረብ መብት
መረጃዎን ለማስኬድ ወይም መብቶችዎን ለመጠበቅ እና ለማስከበር ስለኛ ጥርጣሬ ካለዎት በአገርዎ ውስጥ ላለ ስልጣን ላለው የቁጥጥር ባለስልጣን ቅሬታ የማቅረብ መብት አልዎት።
የሩስያ ፌደሬሽን ዜጋ ከሆኑ ወይም በሩሲያ ፌዴሬሽን ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ የቁጥጥር ባለስልጣን አድራሻዎችን በፌዴራል አገልግሎት የመገናኛ መረጃ ቴክኖሎጂ ቁጥጥር እና የመገናኛ ብዙሃን (Roskomnadzor) ድረ-ገጽ ላይ ያገኛሉ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ዜጋ ከሆኑ ወይም በአውሮፓ ህብረት ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ የተቆጣጣሪ ባለስልጣን አድራሻዎችን በአውሮፓ መረጃ ጥበቃ ቦርድ ድረ-ገጽ European Data Protection Board ላይ ያገኛሉ።
የአውሮፓ ህብረት ዜጋ ወይም የሌላ ሀገር ነዋሪ ከሆኑ በዚህ ሀገር ስልጣን ባለው ባለስልጣን ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ላይ የተቆጣጣሪ ባለስልጣን አድራሻዎችን ያገኛሉ።
8.9. የመረጃ ርዕሰ ጉዳይን ለመለየት የሚያስፈልግ ተጨማሪ መረጃ ስለመጠየቅ
ያቀረቡት መረጃ መብቶችዎን ለመጠበቅ በቂ ካልሆነ፣ ማንነትዎን ለማረጋገጥ ተጨማሪ መረጃ ከእርስዎ ልንጠይቅ እንችላለን።
በጣም አስፈላጊ የሆነውን አስፈላጊ መረጃ ብቻ ለመጠየቅ የተቻለንን እናደርጋለን።
ተጨማሪ መረጃ ማቅረብ ካልቻሉ መብቶችዎን ማክበር አንችልም።
ተጨማሪ መረጃ በመጠየቅ መብቶችዎን እንደጣስን ካመኑ፣ ለሚመለከተው ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ።
8.10. በመብቶችዎ ላይ መረጃ የማቅረብ ውሎች
መብቶችዎን ስለማክበር መረጃን በነጻ እናቀርባለን።
ጥያቄዎ በግልጽ ካልተረጋገጠ ወይም ከመጠን በላይ ከሆነ (በተለይም በመደጋገም ምክንያት) የተጠየቀውን መረጃ ለማቅረብ ልንመልስ ወይም ክፍያ ልንከፍል እንችላለን።
8.11. በመብቶዎ ስለመጠቀም
መብቶዎን እንዲጠቀሙ የምንናቀርባቸው ዘዴዎች
1) የእርስዎን የግል መረጃ ጥበቃ በተመለከተ ጥያቄ ለመላክonline feedback form መጠቀም ይችላሉ፡፡
2) በግል መለያዎያለእርዳታ መብቶችዎን መጠቀም ይችላሉ፡፡
3) በክፍል 13 "ያግኙን" ውስጥ በተጠቀሰው ዘዴ በመጠቀም ወሳኝ ጉዳዮችን በቀጥታ የመረጃ ጥበቃን የሚመራውን ሰው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
8.12. መብትዎን እንዳንጠብቅ ስለሚያደርደርጉ ጉዳዮች
ግዴታዎቻችንን በተመለከተ የሚመለከተው የሕግ አካል በሚፈለግበት ጊዜ መብቶችዎን ልንገድብ እንችላለን።
የእርስዎ የግል መረጃ ጥቅም ላይ በሚውልበት ውቅት እነዚህ ገደቦች ተፈጻሚ ሊሆኑ ይችላሉ፣
1) የብሔራዊ ደህንነት ጥበቃ፣
2) ለመከላከል፣
3) ለህዝብ ደህንነት፣
4) በቅድመ ምርመራ፣ በምርመራ፣ በማንነት ማረጋገጫ ወይም በወንጀል ክስ ሲመሰረት ወይም የወንጀል ቅጣቶችን ለመፈጸም፤ በሕዝብ ደህንነት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መጠበቅ እና መከላከልን ጨምሮ፡፡
5) እርስዎ ለሚኖሩበት ግዛት ህጋዊ አጠቃላይ የህዝብ ጥቅም ዓላማዎች በተለይም የገንዘብ፣ የበጀት ወይም የግብር ጉዳዮች፣ የህዝብ ጤና ወይም ማህበራዊ ደህንነትን ጨምሮ አስፈላጊ ኢኮኖሚያዊ ወይም ፋይናንሺያል ጉዳዮች፡፡
6) የዳኝነት ነፃነትን እና የፍርድ ሂደቶችን ለመጠበቅ፡፡
7) ቁጥጥር ለሚደረግባቸው ሙያዎች የስነምግባር ጥሰቶችን ለመከላከል፣ ለመመርመር፣ ለማጣራት እና ለህግ ለማቅረብ፡፡
8) ከኦፊሴላዊው ባለስልጣን አጠቃቀም ጋር የተገናኘ የክትትል ፣ የምርመራ ወይም የቁጥጥር ተግባር፡፡
9) የመረጃውን ባለቤት ወይም የሌሎችን መብቶች እና ነጻነቶች ለመጠበቅ፡፡
10) የፍትሐ ብሔር ህግ ጥያቄዎችን የማቅረብ ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን የማስፈፀም መብትን ለመጠቀም።
መብቶችዎ እንዲተገበሩ መሟላት ያለባቸው ልዩ ሁኔታዎች፡-
የግል መረጃን ከመሰረዝ መብት ነፃ መሆን፡-
1) ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እና የመረጃ ነፃነትን ማክበር፣
2) በሚመለከተው ሕግ መሰረት የግል መረጃዎችን መጠቀምን ወይም አጠቃላይ የህዝብ ጥቅምን ዓላማን ለማሳካት ወይም በሚመለከተው ሀግ በእኛ ላይ የተጣለውን ኦፊሴላዊ ስልጣንን ለመጠቀም የሚጠይቅ ሀጋዊ ግዴታን መወጣት፣
3) በሕዝብ ጤና አካባቢ የህዝብን ጥቅም መጠበቅ፣
4) ለሕዝብ ጥቅም ፣ ሳይንሳዊ ወይም ታሪካዊ ምርምር ዓላማዎች ወይም ስታቲስቲካዊ ዓላማዎች ለማህደር ለመጠቀም፣
5) ሕጋዊ የይገባኛል ጥያቄን ለማነሳት፣ ለመምራት ወይም ለመከላከል።
መጠቀምን የመገደብ (የማገድ) መብት ነፃ መሆን፡-
1)በእርስዎ ፈቃድ መሠረት ህጋዊ መስፈርቶችን ማስተዋወቅ ፣ ማሟላት ወይም መከላከል፣
2) የሌላ ግለሰብ ወይም ሕጋዊ አካል መብቶችን መጠበቅ፣
3) አስፈላጊ ሕጋዊ የህዝብ ፍላጎቶችን ለማስከበር።
በጥያቄዎ መሰረት መብቶችዎን መጠበቅ ካልቻልን የተረጋገጠ እምቢታ እንልክልዎታለን።
9. ኩኪዎች እና አውቶማቲክ ምዝግብ ማስታወሻዎች
በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ አንቀጽ in Clause 5.2 ላይ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ለማሳካት ኩኪዎችን እና አውቶማቲክ ምዝግብ ማስታወሻዎችን እንጠቀማለን።
ኩኪ በመሳሪያዎ ላይ (ኮምፒተር፣ ታብሌት፣ ስማርት ስልክ፣ ወዘተ) ላይ የተከማቸ ትንሽ የመረጃ ፋይል ነው።
አውቶማቲክ ምዝግብ ማስታወሻ በድር አገልጋዮቻችን እና በደህንነት ስርዓታችን የምንጠቀምበት የምዝግብ ማስታወሻ ፋይል ነው።
ይህንን መረጃ የምናስተናግደው የድረ-ገፃችንን ደህንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀምና አፈፃፀሙን ለማሻሻል ብቻ ነው።
ይህን መረጃ እርስዎን ለመለየት ወይም እነዚህን መረጃዎች ከሌላ መረጃ ጋር ለማዋሃድ አንጠቀምም።
ይህን መረጃ አናስተላልፍም ወይም የተጠቃሚ መገለጫዎችን አንፈጥርም።
እነዚህን ቴክኖሎጂዎች እንዴት እንደምንጠቀም በእኛ "Cookie and automatic logging policy" ውስጥ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።
10. የግል መረጃን ወደ ሶስተኛ ሀገሮች ማስተላለፍን በተመለከተ
የኮንትራክተሩ ሀገር በቂ የሆነ የግል መረጃ ጥበቃ በሚያረጋግጥ ሀገር ዝርዝር ውስጥ ካልተካተተ በአውሮፓ ኮሚሽን፣ በፌዴራል የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቁጥጥር እና የመገናኛ ብዙኃን (Roskomnadzor) እና ብሔራዊ ሕግ በተደነገገው መሠረት መደበኛ የኮንትራት ውሎችን እንጠቀማለን። በምርጥ የደህንነት እና የግላዊነት ልማዶች መሰረት የእርስዎን የግል መረጃ ለመጠበቅ የደህንነት እርምጃዎችን ወስደናል። የእርስዎን መረጃ ለመጠበቅ የደህንነት ጥንቃቄዎችን እንወስዳለን።
11. የመረጃ ደህንነት
የምንሰበስበው እና የምናከማችው የግል መረጃ ሚስጢራዊ መረጃ ነው። በቴክኒካል መሳሪያዎች እና በድርጅታዊ አሠራሮች አማካኝነት ከመጥፋት፣ ከማታለል ወይም ካልተፈቀደ መዳረሻ ይጠበቃሉ፡፡ የመረጃ ጥበቃ ስርዓታችንን ያለማቋረጥ እናሻሽላለን።
በመረጃ ሂደት ወቅት የእርስዎን አደጋዎች በመለየት በመረጃ ጥበቃ ላይ ያለውን ተጽእኖ እንገመግማለን። ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ የደህንነት እርምጃዎችን በመጠቀም የተገኙ ስጋቶችን እንቀንሳለን።
በድረ-ገፃችን ላይ ለግል መለያዎ የምናቀርበውን የይለፍ ቃል የመጠበቅ ሃላፊነት የእርስዎ ነው። ይህን የይለፍ ቃል በምስጢር በመያዝ አለብህ በፍጹም ለማንም መስጠት የለብዎትም።
12. የፖሊሲ ማሻሻያዎች
ይህንን የግላዊነት ፖሊሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ የማሻሻል መብታችን የተጠበቀ ነው።
በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ላይ የተደረጉ ማናቸውንም ለውጦች ያሉትን ሁሉንም መንገዶች በመጠቀም (በምዝገባ ወቅት በቀረበው የኢ-ሜይል ወይም በሚቀጥለው ጉብኝትዎ በድር-ገፃችን ) እናሳውቅዎታለን።
እባክዎ እያንዳንዱን የግላዊነት መመሪያ ፖሊሲ ይገምግሙ።
13. አድራሻ
የግል መረጃ ጥበቃን በተመለከተ መልእክት ለመላክ እባክዎ feedback form
ይጠቀሙ።
በግላዊ መረጃ ጥበቃ ላይ በጣም ወሳኝ ጥያቄዎችን በሚከተለው ኢ-ሜይል የመረጃ ጥበቃ ኦፊሰሩን በቀጥታ ማነጋገር ይችላሉ፡፡
የመጀመሪያ ስም፦ ዲሚትሪ
የመጨረሻ ስም፦ናይሙሺን
ኢ-ሜይል፦privacy@sputniknews.com
እባክዎ ይህ አድራሻ ለግል መረጃ አጠቃቀም እና ጥበቃ ጥያቄዎች ብቻ የሚያገለግል ነው።ተያያዥ ያልሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ አያገኙም፡፡
ከግል መረጃ ጥበቃ ጋር ያልተያያዙ ጥያቄዎችን ለማግኘት እባክዎ ከኤጀንሲው የአድራሻ ዝርዝር Agency’s contact list የሚገኘውን ኢ-ሜይል ይጠቀሙ።
ጥያቄዎን ለሚመለከተው ክፍል ማድረስዎን ያረጋግጡ።
ጥያቄዎን ለተሳሳተ ክፍል ከላኩ ክፍሎቹ በተሰጣቸው ሃላፊነት መሰረት ለጥያቄዎች ምላሽ ስለሚሰጡ ችግርዎ ሳይፈታ ሊቆይ ይችላል፡፡
ለመጨረሻ የዘመነው፦ ቀን/ ወር/ ዓመት
አዳዲስ ዜናዎች
0