- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት እና የደቡባዊው ዓለም የቴክኖሎጂ ሽግግር

የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት እና የደቡባዊው ዓለም የቴክኖሎጂ ሽግግር
ሰብስክራይብ

"[ኢትዮጵያ] በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር ብዛት ሁለተኛዋ ሀገር እንደመሆኗ፣ በአንድ [በጅቡቲ] ወደብ ላይ ጥገኛ መሆን በጣም አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ አሁን ፍላጎታችንና ጥቅማችን በጣም የተለያየ ነው። በዚህም ምክንያት ተጨማሪ ወደቦችን መጠቀም፣ መመልከት ወይም መፈለግ እጅግ አስፈላጊ ነው።" ሲሉ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር የሆኑት አቶ በላይ በየነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ የሁለት ክፍል ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በርበራን ከጎበኘ በኋላ፣ የኢትዮጵያን እየተለወጠ የመጣውን የባህር ላይ እና የጂኦ-ፖለቲካ ስትራቴጂ እንመረምራለን። ይህ ለረጅም ጊዜ በአንድ ኮሪደር ላይ ብቻ ጥገኛ ለነበረችው የየብስ ተከብቦ ሀገር ምን መልዕክት ያስተላልፋል? በሥርዐተ-ንግድ ጥንካሬ፣ በቀጣናዊ ዲፕሎማሲ እና በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ላይ ምን ዓይነት አዲስ ቅርፅ ሊፈጥር ይችላል? ስንል በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር ከሆኑት ከአቶ በላይ በየነ ጋር በዝርዝር እንቃኛለን።
በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ በደቡባዊው ዓለም ወስጥ በመካሄድ ላይ ስላለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢ- ሞቢሊቲ) አብዮት እንዳስሳለን። ለዚህም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመካኒካል፣ ኬሚካል እና ማቴሪያል ሳይንስ ምህንድስና ኮሌጅ ዲን ከሆኑት ከዶ/ር ሽመልስ ለማ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0