- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የመገንባት እቅድ

የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የመገንባት እቅድ
ሰብስክራይብ
“ለዓመታት በአፍሪካ ውስጥ ስንጠቀምባቸው የቆዩትን መረጃዎች (Data) የሀገር በቀል ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም የ-AI ሞዴሎች የሚቀረጹት በሰለጠኑበት መረጃ ልክ ነው። ያ መረጃ በብዛት የመነጨው ከሰሜናዊው የዓለም ክፍል ስለሆነ፣ የሚያንጸባርቀው የእነሱን ማንነት እንጂ የእኛን አይደለም። ስለዚህ በራሳችን መረጃዎች የተደራጀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሊኖረን ይገባል።” ሲሉ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ የሆኑት ረዳት ፕ/ር አደራጀው ምህረት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ ከሆኑት ከረዳት ፕ/ር አደራጀው ምህረት ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ልዩ የሆነ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም ያላትን እቅድ የምንመለከት ሲሆን፤ በሁለተኛው ክፍልም የ2026ቱ የTenDX አዲስ አበባ ጉባኤ ላይ ተገኝተን ስለ ዲጂታል የክፍያ ስርዓቶች፣ ዲጂታል መታወቂያ እና ፓን-አፍሪካዊ የፋይናንስ መሠረተ ልማቶች በካምፓስ ፕላስ ቴክኖሎጂስ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ም/ል ፕሬዝዳንት እና ም/ል ማኔጂንግ ዳ/ር የሆኑትን አዲል አህመድን እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ የባለድርሻ አካላት ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑትን ሳሚናስ ሰይፉን አነጋግረናቸዋል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0