- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ኃይል ወይስ ሕግ፦ ተመድ አሁንም በሕግ የሚመራ ተቋም ነውን?

ኃይል ወይስ ሕግ፦ ተመድ አሁንም በሕግ የሚመራ ተቋም ነውን?
ሰብስክራይብ

“የቪቶ (ድምፅን በድምጽ የመሻር) ስልጣን ያለአግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፤ ተበድሏልም። በ2003 በኢራቅ ላይ በአሜሪካ ጥቃት ሲሰነዘር ሩሲያ ለዚያ ወረራ እና ወታደራዊ ጣልቃገብነት ድምፅ አልሰጠችም። […] አፍሪካ በ2026 ያላትን ቋሚ ያልሆኑ መቀመጫዎች ብንመለከት እንኳ፣ የቪቶ ስልጣን ባላቸው አምስቱ ቋሚ አባላት እና የቪቶ ስልጣን በሌላቸው ቋሚ ባልሆኑ አባላት መካከል ያለው ልዩነት ምንም አይነት ትርጉም አይሰጥም። ይህ ሁኔታ በእውነቱ ዓለም አቀፍ ህግን መሳቂያ ያደርገዋል።” ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሌጅ ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ራስ አድቮኬት ሲፎ ማንቱላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የቬንዙዌላን ጉዳይ ማዕከል አድርገን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሁንም በሕግ የሚመራ ተቋም ነው—ወይስ ዓለም አቀፋዊ አስተዳደር የኃይል እና የመራጭነት (አድሏዊ) አፈጻጸም ጨዋታ ሆኗል? የሚለውን ጥያቄ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሌጅ ውስጥ ተመራማሪ ከሆኑት ከራስ አድቮኬት ሲፎ ማንቱላ ጋር በሰፊው እንመረምራለን። በተጨማሪም አንዳንድ አገራት ማዕቀብ ተጥሎባቸው ሕጋዊነታቸው እንዲታጣስ ሲደረግ፣ ሌሎች ደግሞ ጥበቃ የሚደረግላቸው ስለምንድን ነው? ይህስ በጂኦ-ፖለቲካዊ ሽኩቻ በተቀረጸው ዓለም ውስጥ ስለ ሉዓላዊነት ምን ይነግረናል? የሚሉትንም ጥያቄዎች እንዳስሳለን፡፡
እንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
አዳዲስ ዜናዎች
0