- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የባህል ኃይል፦ ባሕላዊ አመራር፣ ፋሽን እና የአፍሪካ የወደፊት ጉዞ

የባህል ኃይል፦ ባሕላዊ አመራር፣ ፋሽን እና የአፍሪካ የወደፊት ጉዞ
ሰብስክራይብ
“የዓለም አቀፍ ሕግ፣ በምዕራባውያን ወገን ሕጎች የሚጥሱትን እንዲታሰሩ የሚያደርግ ነው። አንድ አፍሪካዊ መሪ በፖለቲካዊ መልኩ የአፍሪካን መንገድ ለመከተል ከወሰነ፣ ኢላማ ይደረጋል። በአንተ ላይ መጥፎ የሆኑ ስሞችን በመለጠፍ መገናኛ ብዙኃንን ተጠቅመው ሕዝቡ አንተን በመጥፎ ዓይን እንዲመለከትህ ማድረግ ይጀምራሉ። ይህንንም በአንተ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ትክክለኛ እንደሆነ ለማስመስል ይጠቀሙበታል። እስካሁንም ያለው አካሄድ ያው ነው።” ሲሉ በጋና ባሕላዊ መሪ እና የ‘ዘ ቴስት ኦፍ አፍሪካ’ ተባባሪ መስራች የሆኑት ቴንጎል ኬፕሌማኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ በጋና ባሕላዊ መሪ እና የ‘ዘ ቴስት ኦፍ አፍሪካ’ ተባባሪ መስራች እና የ‘ካልቸራል ዋንነስ ፌስቲቫል’ አዘጋጅ ቴንጎል ኬፕሌማኒ ጋር በመሆን — በፍጥነት እየተለወጠ ባለው ዓለም ውስጥ የአፍሪካ ወጎች እንዴት አግባብነታቸውን ጠብቀው ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የ‘አፍሪካ ሞዛይክ’ የፋሽን መድረክን አስታከን ከኢትዮጵያ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና ከታዋቂው ሙዚቀኛና አርቲስት ስለሺ ደምሴ (ጋሼ አበራ ሞላ) ጋር ስለ ባህል ዲፕሎማሲ እና ተያያዥ ጉዳዮች ያደረግነውን ቆይታ አካትተናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0