- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

አፍሪካን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን፡- ሉዓላዊነት እና ደህንነት

የአፍሪካ ዲጂታል ሉዓላዊነት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ደህንነት እና ገለልተኛ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ሥርዓት ግንባታ
ሰብስክራይብ
''አፍሪካ ከውጭ በሚገቡ ቴክኖሎጂዎች ላይ ብቻ ጥገኛ ከመሆን ወጥታ፤ የራሷን የመረጃ ማዕከላት በመገንባት፣ ገለልተኛ የፍተሻ ላቦራቶሪዎችን በማቋቋም እና ሕጋዊ የማረጋገጫ ሥርዓት በመዘርጋት ዲጂታል ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ አለባት፤'' ሲሉ ናይጄሪያዊው የዲጂታል አስተዳደር እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፖሊሲ ባለሙያ ቪክቶር ፋሙቦዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው ተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን ፤ የራስ-ገዝ AI ሲስተሞች የደህንነት መቆጣጠሪያዎችን (Sandboxes) ጥሰው በመውጣት የሚፈጥሩት መዋቅራዊ የሳይበር ስጋት፣ በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ የሚፈጠር የሕግ ተጠያቂነት ክፍተት፣ የግዙፍ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ፈጣን የገበያ ውድድር በደህንነት ፍተሻ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ፣ በአፍሪካ የግዙፍ የመረጃ ማዕከላት እጥረት የሚያስከትለው ተጋላጭነት እንዲሁም አፍሪካውያን ሀገራት በራሳቸው ባለሙያዎችና ሕጎች የሚመራ ገለልተኛ የAI መፈተሻ እና የማረጋገጫ ሥርዓት መገንባት ስለሚችሉበት ስትራቴጂካዊ መንገድን ከቪክቶር ፋሙቦዴ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0