- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA)፣ የሴቶች ኢንተርፕራይዞች ዕድገት እና የኢንዱስትሪ ሽግግር

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA)፣ የሴቶች ኢንተርፕራይዞች ዕድገት እና የኢንዱስትሪ ሽግግር
ሰብስክራይብ

"ሴቶች ለኢኮኖሚና ለኢንዱስትሪ ዕድገት ያላቸው ፍላጎትና ዝግጁነት ከፍተኛ ነው፤ ነገር ግን ከባንክ ብድርና ከፋይናንስ አቅርቦት ጀምሮ እስከ አውቶማቲክ ማሽነሪዎችና የመስሪያ ቦታዎች ድረስ ያሉ መዋቅራዊ ማነቆዎች በግልጽ ሊፈቱ ይገባል፤" ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ አምራች ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አመለወርቅ ኃይለስላሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) አህጉራዊ የንግድ ትስስርን መነሻ በማድረግ፣ የአፍሪካ ሴቶች አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ወደ አውቶማቲክና ለወጪ ንግድ ብቁ ወደሆኑ ግዙፍ ፋብሪካዎች የማሸጋገር ስትራቴጂን፣ ከመያዣ ነፃ የሆነ የፋይናንስ አቅርቦትና የትብብር አውታሮችን የማጠናከር ሂደትን፣ የሀገር ውስጥ ጥጥና ግብርና ምርቶች ላይ የእሴት ጭማሪ የማድረግ ጥረቶችን፣ በፋብሪካዎች ውስጥ የህፃናት ማቆያዎችን በማቋቋም እናቶችን የመደገፍና የትውልድ ግንባታ ሚናን፣ እንዲሁም የሴት መሪዎችን የስራና የግል ህይወት ሚዛን የማስጠበቅ ተግባራዊ ስልቶችን በጥልቀት ተንትነናል።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0