- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የጂኦ ፖለቲካ ሽግግሮች እና የአገር በቀል አረንጓዴ ቴክኖሎጂ መዋቅራዊ ሉዓላዊነት

የጂኦፖለቲካዊ ሽግግሮች እና የአገር በቀል አረንጓዴ ቴክኖሎጂ መዋቅራዊ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ
''የዩክሬን ቀውስ በአንድ ጀምበር የተከሰተ ሳይሆን ምዕራባውያን የአንድዮሽ የበላይነታቸውን ለማስቀጠል እና ዓለም ወደ ብዙሃን የኃይል ማዕከል እንዳትቀየር የጠነሰሱት የረጅም ጊዜ የውክልና ጦርነት ውጤት ነው'' ሲሉ የህግ ባለሙያው አቶ ዳንኤል ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በምዕራባውያን የሚመራው ኔቶ እና የአውሮፓ ህብረት ከ2014ቱ የኪየቭ መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ ግጭቱን እንዴት እንደጠነሰሱት፣ እንዲሁም የሰላም ስምምነቶችን (Minsk Agreements) የፈረሙት ለሰላም ሳይሆን ዩክሬንን በሩሲያ ላይ የጦር ጥቃት ለመፈጽም፣ ለማደራጀትና ጊዜ ለመግዛት እንደነበረ ምዕራባውያን ልሂቃን ራሳቸው ያመኑበትን እውነታ የጂኦፖለቲካ እና የህግ እይታዎችን መነሻ በማድረግ ከህግ ባለሙያ አቶ ዳንኤል ፍቃዱ ጋር ጥልቅ ትንተና አድርገናል።

በክፍል ሁለት ደግሞ፣ አፍሪካ የሌሎችን እርዳታ ሳትጠብቅ በራሷ የግብርና ሃብትና በአገር በቀል ኢንጂነሪንግ እውቀት ራሷን ወደ ላቀ ምዕራፍ የምታሸጋግርበትን ታሪካዊ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ አብዮት እንቃኛለን። የኢትዮጵያው "አገልግል ኢኮ-ፓኬጂንግ" የግብርና ተረፈ ምርቶችን በአገር ውስጥ ማሽነሪዎች በመቀየር ርካሽ ፕላስቲኮችን እንዴት እየተካ ይገኛል? እንደ ብሪክስ ሴቶች ቢዝነስ አሊያንስ ያሉ የደቡብ-ደቡብ ጥምረቶችን በመጠቀምስ አገር በቀል የቴክኖሎጂ ፈጠራን ወደ ህንድ እና ደቡብ አፍሪካ ለማሻጋር ምን ዓይነት ስልታዊ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው? በሚሉት አበረታች ነጥቦች ዙሪያ ከተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ተባባሪ መስራች አፎሚያ አንዱአለም ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0