- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የምስራቅ አፍሪካ የንግድ ስነ-ህንጻ እና 'ጄነሬቲቭ ኤአይ' መዋቅራዊ ሉዓላዊነት

የምስራቅ አፍሪካ የንግድ ስነ-ህንጻ እና ጄነሬቲቭ ኤአይ መዋቅራዊ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ
''የንግድ ሂደቶች በቴክኖሎጂ ሲታገዙ እና ወረቀት አልባ አሰራር ሲሰፍን የንግድ ወጪን ከ10 እስከ 30 በመቶ በመቀነስ አህጉራዊ ትስስርን ማረጋገጥ ይቻላል'' ሲሉ የምጣኔ ሀብት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አሸናፊ ተሾመ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ ከ118 ዓመታት ረጅም ታሪክ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጸደቀው የኢትዮጵያ ወጥ ብሄራዊ የንግድ ፖሊሲ፣ ድንበር አካባቢ ያሉ አሰልቺ የኬላዎችና የቢሮክራሲ ማነቆዎችን በማስቀረት ሀገሪቱን ለታላቁ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ውድድር እንዴት ያበቃታል? የሎጂስቲክስ፣ የባንክ እና የቴሌኮም ዘርፎችስ ከአህጉራዊ ኩባንያዎች ጋር አጋርነት ፈጥረው የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያመጡ ምን ዓይነት መዋቅራዊ ዕድሎችን ይዞ መጥቷል? ስንል ከአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አሸናፊ ተሾመ ጉታ ጋር ሰፊ ቆይታን አድርገናል።

በክፍል ሁለት ደግሞ፣ በረቀቀው የቴክኖሎጂ ዘመን የአፍሪካን የዲጂታል መረጃ ሉዓላዊነት እና ሳይንሳዊ ነፃነት በራስ አቅም የማስከበር ወሳኝ ጉዳይ ላይ አተኩረናል። የሰው ሰራሽ አስተዋፅዖ (Generative AI) ቴክኖሎጂ የአፍሪካን ባህል፣ የፊልም ኢንዱስትሪ፣ የቋንቋ ብዝሃነት እና የሀገር በቀል ዕውቀቶችን ጠብቆ ለማቆየትና ለማበልጸግ እንዴት ጥቅም ላይ መዋል አለበት? ወጣቶቻችንስ የስራ ፈላጊነትን አስተሳሰብ ሰብረው የራሳቸውን እሴት ወደ መፍጠር እንዲሸጋገሩ ምን መደረግ አለበት? በሚሉት ስልታዊ ነጥቦች ዙሪያ ከጄኔሬቲቭ ኤ አይ የፈጠራ ሥራዎች ዳይሬክተር ብርሃን ታፈሰ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0