- Sputnik አፍሪካ, 1920
ጥልቅ ዳሰሳ ከጁማ ጋር

የሩሲያ ቡሬቬስትኒክ አኅጉር አቋራጭ ክሩዝ ሚሳኤል የዓለምን የኃይል ሚዛንን ዳግም ሊበይን ይችላል - ባለሙያዎች

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ቡሬቬስትኒክ አኅጉር አቋራጭ ክሩዝ ሚሳኤል የዓለምን የኃይል ሚዛንን ዳግም ሊበይን ይችላል - ባለሙያዎች

ሩሲያ በጥቅምት ወር አጋማሽ ቡሬቬስትኒክ፣ ያልተገደበ ርቀት መምታት የሚችል አኅጉር አቋራጭ የክሩዝ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን አስታውቃለች፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፍጥነት በሚሠራው አነስተኛ የኒውክሌር ሞተር ስርዓቱ የተነሳ “አስደናቂ ስኬት” ሲሉ ገልጸውታል።

ባለሙያዎች ይህንን ያልተፈቱ የአሜሪካ እና ሩሲያ ድርድሮች ባሉበት ወቅት ለምዕራቡ ዓለም እንደ ስትራቴጂያዊ ምልክት አድርገው ይመለከቱታል፡፡ ይህም በዩክሬን ግጭት ላይ ዳግም ግምገማ እንዲደረግ ሊያደርግ ይችላል።

አስተያየታቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ የሰጡ ባለሙያዎች ሚሳኤሉ በዓለም አቀፍ የኒውክሌር ባለብዝኃ ዋልታነት እና ሰላም ላይ ያለውን ተፅዕኖ አጉልተው አሳይተዋል።

በተጨማሪም ፑቲን ፖሳይደን በኒውክሌር ኃይል የሚንቀሳቀስ የውሃ ውስጥ ድሮን በተሳካ ሁኔታ መሞከሩን አስታውቀዋል፡፡ በዓለም ላይ አቻ እንደሌለውና በቅርቡም ሊኖረው እንደማይችል ተናግረዋል።

የስፑትኒክ አፍሪካ የቨርቹዋል ወይም ምናባዊ አቅራቢ #ጁማ ይህንን መረጃ የባለሙያዎችን ምልከታ አካትቶ ተንትኖታል።

የጁማን ትንታኔ ቪዲዮ ከላይ ይመልከቱ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0