- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) አዲስ ምዕራፍ፣ የሀገር ውስጥ ምንዛሬ ክፍያ (PAPSS) እና የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) አዲስ ምዕራፍ፣ የሀገር ውስጥ ምንዛሬ ክፍያ (PAPSS) እና የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ

አፍሪካ ከራሷ ይልቅ ከተቀረው ዓለም ጋር ይበልጥ የተሳሰረች ሆና ቆይታለች፤ በአውሮፓ የእርስ በርስ ንግድ ከ60 በመቶ በላይ ሲሆን በአፍሪካ ግን በ15 በመቶ አካባቢ ነው። አዲሱን ፍልስፍና ስንቀርጽ የጨዋታውን ሕግ ራሳችን ማውጣት፣ ለታዳጊ ኢንዱስትሪዎቻችን ከለላ መስጠትና በራሳችን የክፍያ ሥርዓት መገበያየት አለብን፤" ሲሉ

የኢኮኖሚ ባለሙያውና የማኅበራዊ-ኢኮኖሚ ፖሊሲ ተመራማሪው ዶ/ር መስፍን ሙሉጌታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ አፍሪካ ከምዕራባውያን የኢኮኖሚ ንድፎች ወጥታ ራሷን የቻለች ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት የምትገነባበትን አዲስ ሥርዓት መነሻ በማድረግ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) እና እንደ ሎቢቶ እና ላፕሴት (LAPSSET) ያሉ የመሠረተ ልማት ኮሪደሮች ለሀገር ውስጥ እሴት መጨመር ያላቸውን ፋይዳ፣ በሀገር ውስጥ ምንዛሬ መገበያየት የሚያስችለውን የፓን አፍሪካ የክፍያ ሥርዓት (PAPSS) ዕድሎችና ተግዳሮቶች እንዲሁም በብዝኃ-ዋልታ ዓለም የብሪክስ (BRICS+) እና የደቡብ-ለደቡብ ትብብርን በጥቅም ላይ ስለማዋል ከኢኮኖሚ ባለሙያውና የማኅበራዊ-ኢኮኖሚ ፖሊሲ ተመራማሪው ዶ/ር መስፍን ሙሉጌታ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0