- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የአፍሪካ የቀዶ ህክምና ሉዓላዊነት፣ የጤና ሥርዓት ጽናት እና አህጉራዊ የክሊኒካል አቅም ግንባታ

የአፍሪካ የቀዶ ህክምና ሉዓላዊነት፣ የጤና ሥርዓት ጽናት እና አህጉራዊ የክሊኒካል አቅም ግንባታ
ሰብስክራይብ
"ደህንነቱ የተጠበቀ የቀዶ ህክምና ለመስጠት ደህንነቱ የተጠበቀ ማደንዘዣ፣ የባዮሜዲካል ምህንድስና፣ ላቦራቶሪ፣ አስተማማኝ የደም ልገሳ እና የማጣሪያ አገልግሎት ያስፈልጋል፤ እነዚህ ግብዓቶች ታካሚዎችን ብቻ ሳይሆን እንደ ኮቪድ-19 ባሉ ወረርሽኞች ወቅት ሌሎች ታካሚዎችንም የሚያድኑ የጤና ሥርዓቱ የጀርባ አጥንት ናቸው። ያለ ጤና ምንም ዓይነት ልማት ሊኖር አይችልም፤" ሲሉ የፓን-አፍሪካ የቀዶ ህክምና ጤና አጠባበቅ ፎረም የሥራ አስፈጻሚ አባልና የአጋርነት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ኢማኑኤል ማላቦ ማካሳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ በአዲስ አበባ ከህዳር 10 እስከ 12 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 19 እስከ 21 ቀን 2026) የተካሄደውን 4ኛውን የፓን-አፍሪካ የቀዶ ጥገና ጤና አጠባበቅ ፎረም መነሻ በማድረግ፤ አፍሪካ ከውጭ ጥገኝነት ተላቃ የራሷን የቀዶ ጥገና ጤና ሥርዓት የምትገነባበትን አህጉራዊ ማዕቀፍ፣ በወረዳና በገጠር ሆስፒታሎች የሚታየውን የመሠረተ ልማትና የባለሙያ እጥረት፣ የሀገር ውስጥ ፋይናንስ አቅም ማሳደግን፣ በመረጃ የተደገፈ የፖሊሲ አተገባበርን፣ በደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ (SADC) ቀጣናዊ ትብብርንና ሀገር በቀል የባህላዊ ህክምና እውቀቶችን መሰነድ እንዲሁም በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) በኩል የ55ቱን ሀገራት ፖሊሲ ማቀናጀትን አስመልክቶ በጥልቀት ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0