- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የሼንዘኑ የኤፔክ ጉባኤ፣ የሦስቱ ኃያላን ሀገራት መሪዎች ታሪካዊ ውይይት እና ለአፍሪካ የሚኖረው የኢኮኖሚና የንግድ ዕድል

የሼንዘኑ የኤፔክ ጉባኤ፣ የሦስቱ ኃያላን ሀገራት መሪዎች ታሪካዊ ውይይት እና ለአፍሪካ የሚኖረው የኢኮኖሚና የንግድ ዕድል
ሰብስክራይብ
"የእስያ-ፓስፊክ አባል ሀገራት የዓለምን ከፍተኛ የኢኮኖሚና የንግድ ድርሻ የሚይዙበት እና ቻይና በቴክኖሎጂ ማዕከልነቷ በሼንዘን እያስተናገደችው ያለው የኤፔክ ጉባኤ ለዓለም ገበያ መረጋጋት ወሳኝ ነው። ከዚህም በላይ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ እና በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መካከል የሚደረገው የሦስትዮሽ ውይይት ለባለብዙ-ዋልታ ዓለም ሥርዓት እና ለንግድ ማዕቀቦች ማርገብ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ታሪካዊ ክስተት ነው፤" ሲሉ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪው ሙስጠፋ አብደላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ በሼንዘኑ የAPEC ጉባኤ ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ፣ የቴክኖሎጂና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ትብብር፣ እንዲሁም የሦስቱ ኃያላን መሪዎች ታሪካዊ መገናኘት ለዓለም የነዳጅ ዋጋ፣ ለፋይናንስ ገበያ እና ለጂኦፖለቲካ መረጋጋት የሚያስተላልፈውን መልእክት በጥልቀት ተወያይተናል። በተጨማሪም ይህ ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ሽግግር እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ የሚፈጥራቸውን የንግድ ዕድሎች ዳስሰናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0