- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የብሪክስ + አዲስ የኢኮኖሚ ምህዳር እና የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት

የብሪክስ + አዲስ የኢኮኖሚ ምህዳር እና የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ

''አፍሪካውያን የቀደሙትን የቅኝ ግዛት የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ መስመሮች በመስበር፣ የራሳቸውን የኢንዱስትሪና የንግድ ካርታ መዘርጋት አለባቸው። በሃይል አቅርቦትና በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ መንግሥት የሚጫወተው መሪ ሚና ለግሉ ዘርፍ ማደግ አስፈላጊውን መሠረት ይጥላል። እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ የኃይል ፕሮጀክቶች ደግሞ የአንድ ሀገር ብቻ ሳይሆኑ የመላው ቀጣናችን የኢንዱስትሪ መፋጠኛ ናቸው፤'' ሲሉ ልማታዊ ኢኮኖሚስቱና የቀድሞ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለካቸው ስሜ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ዝግጅታችን፤ የBRICS+ አዲስ የምዕራባውያን ያልሆነ የኢኮኖሚ ምህዳርን፣ የኃይል ዲፕሎማሲና የህዳሴ ግድብን አህጉራዊ ፋይዳ፣ የቅኝ ግዛት ዘመን የሎጂስቲክስ ካርታዎችን በመስበር አህጉራዊ ንግድን የማስፋፋት ስትራቴጂን፣ ከስዊፍት ውጪ ያሉ የሃገር ውስጥ ገንዘቦችን የክፍያ አማራጮች፣ እንዲሁም የዳያስፖራውን እውቀትና ካፒታል ለኢንዱስትሪ ዕድገት የመጠቀም መንገዶችን ከእንግዳችን እንዳለካቸው ስሜ (ዶ/ር) ጋር በሰፊው ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0