የኢትዮጵያን የቆዳ ምርቶች በአፍሪካ አኅጉርና ከዚያም ባሻገር ለማስተዋወቅ እንሠራለን - የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማዕከል መሥራች

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያን የቆዳ ምርቶች በአፍሪካ አኅጉርና ከዚያም ባሻገር ለማስተዋወቅ እንሠራለን - የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማዕከል መሥራች

 

ኢትዮጵያውያን የቆዳ አምራቾች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰፊ መረብ በአግባቡ እየተጠቀሙ አይደለም የሚሉት የማዕከሉ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ንግሥት ኃይሌ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

 

አየር መንገዱ እሴት የተጨመረባቸውን የቆዳ ውጤቶች በቀጥታ ወደ ውጭ ሀገራት ለመላክ ሰፊ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ ከ12ኛው የአፍሪካ ምርት አቅርቦትና ፋሽን ሳምንት ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“...በቆዳ ዘርፍ የተሰማሩ የሴቶች አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በማብቃት እነዚህን ዕድሎች ወደ ተግባር በመቀየር ዘርፉን ወደ ቀጣይ የዕድገት ደረጃ እናሸጋግራለን ብለን በልበ ሙሉነት እናምናለን። በተጨማሪም የኢትዮጵያን የቆዳ ምርቶች በአፍሪካ አኅጉርና ከዚያም ባሻገር ለማስተዋወቅ እንሠራለን።”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0