የብሪክስ ሀገራት በኒውክሌር ኃይል ትብብር ዙሪያ መከሩ - ሮሳቶም

© telegram sputnik_ethiopiaየብሪክስ ሀገራት በኒውክሌር ኃይል ትብብር ዙሪያ መከሩ - ሮሳቶም
የብሪክስ ሀገራት በኒውክሌር ኃይል ትብብር ዙሪያ መከሩ - ሮሳቶም - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.11.2026
ሰብስክራይብ

የብሪክስ ሀገራት በኒውክሌር ኃይል ትብብር ዙሪያ መከሩ - ሮሳቶም

ግብፅ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ የብሪክስ እና አጋር ሀገራት የኒውክሌር ኃይል ዘርፍ መሪዎች፤ የኒውክሌር ኃይል ትብብራቸውን ለማጠናከር በቱርክ አንታሊያ ከተማ በተካሄደው "የዓለም አቶሚክ ቀናት" ፎረም ላይ መሰባሰባቸውን የሩሲያው መንግሥታዊ ኮርፖሬሽን ሮሳቶም አስታውቋል።

የስብሰባው ቁልፍ ነጥቦች፦

አዲስ ቻርተር፦ ተሳታፊዎች የብሪክስ የኒውክሌር ኃይል መድረክ ቻርተርን የሚያጸድቅ ፕሮቶኮል በይፋ ፈርመዋል።

ስትራቴጂካዊ ዕቅዶች፦ የመድረኩ ዋና አስተባባሪ ኤልሲ ፑሌ የ2026 ስኬቶችን በመገምገም፤ የ2027ቱን የሥራ ፍኖተ ካርታም ይፋ አድርገዋል።

ፋይናንስ እና የአቅርቦት ሰንሰለት፦ ባለሙያዎች በባለብዙ ወገን ተቋማት በኩል የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት በሚቻልባቸው መንገዶች እና ለግዙፍ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ዘላቂ የአቅርቦት ሰንሰለት በመገንባት ዙሪያ አዳዲስ ጥናቶችን አቅርበዋል።

የኒውክሌር ኃይል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የኃይል ሽግግርን ለማፋጠን እና ጂኦፖለቲካዊ አለመረጋጋትን በአንድ ጊዜ ለመቀነስ የሚያስችል ብቸኛው ቴክኖሎጂ ነው ሲሉ የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሲ ሊካቼቭ ፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

"ሮሳቶም ለአጋሮቹ ሁልጊዜ መፍትሔዎችን ሲያቀርብ፣ ዕውቀትና ቴክኖሎጂዎቹን ሲያካፍል ቆይቷል፤ ወደፊትም ይህንኑ አጠናክሮ ይቀጥላል" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0