ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያውን የኢንዱስትሪ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ አስመረቀች
18:45 16.11.2026 (የተሻሻለ: 18:54 16.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያውን የኢንዱስትሪ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ አስመረቀች
የፋብሪካው መቋቋም ወርቅን በጥሬው ወደ ውጭ መላክን በማስቀረት በሀገር ውስጥ ማቀነባበር የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ነው ተብሏል።
በመንግሥት ባለቤትነት ስለሚተዳደረው 'ዲአርሲ ጎልድ ሪፋይነሪ' ቁልፍ ዝርዝሮች፦
መገኛ ቦታ፦ ካሌሚ፣ ታንጋኒካ ግዛት
የማምረት አቅም፦ በወር ከ500 እስከ 600 ኪሎ ግራም ወርቅ የማጣራት አቅም አለው
የምርት ጥራት፦ 99.9% ጥራት ያለው ወርቅ ያመርታል
የምርቱ ዓላማ፦ የሀገሪቱን የወርቅ ክምችት ለማሳደግና ለማጠናከር እንዲረዳ ለኮንጎ ማዕከላዊ ባንክ የሚቀርብ ነው
የወደፊት ዕቅዶች፦ በታላቁ ምሥራቅ ክልል፣ በኪቩ፣ በካሳይ እና በኪንሻሳ ተጨማሪ የኢንዱስትሪ ማጣሪያ ተቋማት ለመገንባት ታቅዷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
