ለፑቲን፣ ሺ እና ትራምፕ የሦስትዮሽ ስብሰባ አጀንዳና የጋራ መግለጫ እየተዘጋጀ ነው - የፑቲን አማካሪ

© telegram sputnik_ethiopiaለፑቲን፣ ሺ እና ትራምፕ የሦስትዮሽ ስብሰባ አጀንዳና የጋራ መግለጫ እየተዘጋጀ ነው - የፑቲን አማካሪ
ለፑቲን፣ ሺ እና ትራምፕ የሦስትዮሽ ስብሰባ አጀንዳና የጋራ መግለጫ እየተዘጋጀ ነው - የፑቲን አማካሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.11.2026
ሰብስክራይብ

ለፑቲን፣ ሺ እና ትራምፕ የሦስትዮሽ ስብሰባ አጀንዳና የጋራ መግለጫ እየተዘጋጀ ነው - የፑቲን አማካሪ

የሩሲያ ፕሬዚዳንት አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ፤ ከኅዳር 9 እስከ 10 በቻይናዋ ሼንዘን በሚካሄደው የእስያ ፓሲፊክ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ጉባኤ ቭላድሚር ፑቲን የሚኖራቸውን ዋና ዋና አጀንዳዎች ዘርዝረዋል።

ቁልፍ ዝርዝሮች፦

🟠 ቭላድሚር ፑቲን፣ ሺ ጂንፒንግ እና ዶናልድ ትራምፕ ኅዳር 10 ከቀኑ 3፡30 በቻይና መሪ መኖሪያ ቤት እንዲገናኙ ታቅዷል። የስብሰባውን አጀንዳና የጋራ መግለጫም እያዘጋጁ ነው። ሩሲያና ቻይና የራሳቸውን ሀሳብ አቅርበው የአሜሪካን ምላሽ እየጠበቁ ነው።

🟠 በተጨማሪም በሩሲያና በአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች መካከል የሁለትዮሽ ስብሰባ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የዩክሬን ጉዳይም ከሚነሱት ርዕሰ ጉዳዮች መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል።

🟠 ፑቲንና ሺ በኃይል አቅርቦት፣ በፋይናንስ፣ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና በሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነቶች ላይ ይወያያሉ። ይህ በዚህ ዓመት የሚያደርጉት አምስተኛ ስብሰባቸው ይሆናል።

🟠 በሥራ የቁርስ መርኃ-ግብር ወቅት ፑቲን በአቡዳቢ የድርድር ሂደት ዙሪያ ለሺ መረጃ ያቀርባሉ። ድርድሩን ለመቀጠል ስምምነት ላይ ቢደረስም የሦስትዮሽ ውይይቱ የሚካሄድበት ቀን ገና አልተወሰነም።

🟠 ፑቲን ኅዳር 9 በእስያ ፓሲፊክ የኢኮኖሚያዊ ትብብር የዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ ላይ ከሺ በመቀጠል ንግግር ያደርጋሉ። ከ30 በላይ የሩሲያ የንግድ ዘርፍ ተወካዮችና ኩባንያዎችም በጉባኤው ይሳተፋሉ።

🟠 ሩሲያ በ2035 የአፔክ ጉባኤን ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን ጥያቄዋ እንደሚጸድቅም ተስፋ አድርጋለች።

🟠 የጉባኤው ዋና ክፍል ኅዳር 10 የሚካሄድ ሲሆን ከ2027 እስከ 2035 በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ የሚኖረውን ትብብር የሚያመለክት የመጨረሻ መግለጫ ይጠበቃል።

🟠 ፑቲን ከቬትናም የኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ ቶ ላምና ከታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አኑቲን ቻርንቪራኩል ጋር እንደሚገናኙ ይጠበቃል። ከሌሎች መሪዎችም ጋር መደበኛ ያልሆኑ ውይይቶችን ያደርጋሉ።

የሩሲያ ፕሬዚዳንት የቻይና ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከታጂኪስታን ፕሬዚዳንት ኢሞማሊ ራህሞን ጋር የሥራ ስብሰባ ለማድረግ ወደ ዱሻንቤ እንደሚያቀኑ ኡሻኮቭ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0