- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

ከሕክምና ተቋማት ባሻገር፦ በአፍሪካ የስኳር በሽታ ሕክምና እውነታዎች

ከሕክምና ተቋማት ባሻገር፦ በአፍሪካ የስኳር በሽታ ሕክምና እውነታዎች
ሰብስክራይብ

“"በኢትዮጵያ ከስኳር ህመም ጋር ከሚኖሩ ሰዎች መካከል 76.4% ያህሉ ህመሙ እንዳለባቸው አያውቁም። ይህም 1.75 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ሳይታወቅባቸው ከበሽታው ጋር እንደሚኖሩ ያሳያል።[...] ወደ ሕክምና ተቋም እንድትሄዱ ልናስገድዳችሁ አንችልም፤ ስለዚህ የጤናችሁ ኃላፊነት በእጃችሁ ነው። ለጤናችሁ ቅድሚያ ስጡ፣ የጤና አገልግሎትን የመፈለግ ባህል ይኑራችሁ፤ በየጊዜውም የጤና ምርመራ አድርጉ '' ሲሉ ዶ/ር ሩት ዳኛቸው፣ የሕክምና እና የህብረተሰብ ጤና ባለሙያ ሳይንስ ለአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም ተናግረዋል።

በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን በፈረንጆቹ ህዳር 14 በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከበረውን የዓለም የስኳር በሽታ ቀንን መሠረት በማድረግ ከሕክምና ተቋማት ባሻገር፦ በአፍሪካ የስኳር በሽታ ሕክምና ፋይናንስን ማረጋገጥና በግሎባል ሳውዝ የጤና ፍትሃዊነትን ማስፈንን በሚመለከት እንዳስሳለን።

የሕክምና በህብረተሰብ ጤና ሳይንስ እና በፕሮጀክት ማኔጅመንት ባለሙያ ዶ/ር ሩት ዳኛቸው ደግሞ ሙያዊ ዕይታቸውን ያጋሩናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0