በኢትዮጵያ የሚገኘው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስፑትኒክ ፕሮን ተቀላቀለ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ‘ስፑትኒክ ፕሮ’ን ተቀላቀለ
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ‘ስፑትኒክ ፕሮ’ን ተቀላቀለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.11.2026
ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፉ የዜና ወኪልና ሬዲዮ ስፑትኒክ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስፑትኒክፕሮ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ሥልጠናን ሰጥቷል።
በ‘ስፑትኒክ አፍሪካ’ የከፍተኛ ማህበራዊ ሚዲያ ቪዲዮ ኤዲተር የሆነችው አና ካሊንኪና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም የቪዲዮ ይዘቶችን ስለመፍጠር ንግግር ያደረገች ሲሆን፣ ጋዜጠኞች በዕለት ተዕለት ሥራቸው ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ በጣም ጠቃሚ መሣሪያዎችን አጉልታ አሳይታለች።
በጋዜጠኝነት ሥራ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በኃላፊነት ስሜት መጠቀም ያለውን ጠቃሚነት አፅንዖት የሰጡት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ሁማኒቲስ ኮሌጅ ዲን በልስቲ ጋሻው (ዶ/ር)

“አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰውን የፈጠራ ችሎታ፣ ሂሳዊ አስተሳሰብ፣ ሙያዊ ውሳኔ ሰጪነት ወይም የሥነ ምግባር ኃላፊነት ሊተካ አይገባም። ይልቁንም ችሎታዎቻችንን ለማሳደግ፣ ፈጠራዎቻችንን ለማስፋት እና የሥራችንን ጥራት ለማሻሻል እንደ ኃይለኛ መሣሪያ ልንጠቀምበት ይገባል።” ሲሉ ተናግረዋል።

አዳዲስ ዜናዎች
0