ኢትዮጵያ ከኮፕ-32 በፊት የአየር ንብረት ቃል-ኪዳኖችን ለመተግበር ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቀረበች
20:52 15.11.2026 (የተሻሻለ: 21:44 15.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከኮፕ-32 በፊት የአየር ንብረት ቃል-ኪዳኖችን ለመተግበር ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቀረበች
የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ-32 ዋና ተደራዳሪ ዶክተር ፍጹም አሰፋ፤ በቱርክ አንታሊያ በተካሄደው የኮፕ-31 ጉባኤ ሦስት ዋና ዋና የጎንዮሽ መድረኮች ላይ ባደረጓቸው ንግግሮች ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦
የበጀትና የኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ቅንጅት፦ ቀዳሚ የአየር ንብረት ጉዳዮችን ከብሔራዊ በጀትና ከኢንቨስትመንት ማዕቀፎች ጋር በማቀናጀት፤ የፋይናንስ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ሀብት ማሰባሰብ እና ቃል-ኪዳኖችን ወደ ተግባራዊ የልማት ሥራዎች መቀየር አለባቸው።
ተግባራዊና በቂ ፋይናንስ፦ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፋይናንስ ቃል-ኪዳኖችን የታዳጊ ሀገራትን ትክክለኛ ፍላጎት ወደሚመልስ ተግባራዊ ድጋፍ መቀየር፤ ለዚህም በቂ የፋይናንስ፣ የተጠናከረ ተቋማዊ አቅም እና ውጤታማ የትግበራ ሥርዓት መዘርጋት ።
ቃል-ኪዳኖችን ወደ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መቀየር፦ ሀገራት ቃል-ኪዳኖቻቸውን ወደ ተጨባጭ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መለወጥ እንዲችሉ፤ ብሔራዊ የልማትና የአየር ንብረት ቅድሚያዎችን ከፋይናንስ እና ከቴክኒክ ድጋፍ ጋር ማስተሳሰር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
