ቻይና በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስትመንቷን በእጥፍ ልታሳድግ ነው

ሰብስክራይብ

ቻይና በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስትመንቷን በእጥፍ ልታሳድግ ነው 

 

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ አዳዲስ የቻይና የንግድ ልዑካን ቡድኖችን ከኮርፖሬሽኑ ጋር ለማገናኘት እንደሚሠሩና በኢንዱስትሪ ፓርኮችና ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የቻይናን ኢንቨስትመንት በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በእጥፍ ለማሳደግ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። 

 

አምባሳደሩ ይህን የገለጹት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍጹም ከተማ ጋር ትብብርን በማጠናከር የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በመከሩበት ወቅት ነው። 

 

የቻይና የዲፕሎማሲ ልዑክ መሪ፤ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ሥርዓቷን እንድታጠናክርና የሀገሪቱን ተወዳዳሪነት የሚገድቡ ችግሮችን እንድትፈታ ጠይቀዋል። 

 

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በበኩላቸው፤ ኮርፖሬሽኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የቻይና ባለሀብቶች ድጋፍ ለማድረግና የሥራ እንቅስቃሴያቸውን ለማመቻቸት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0