ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሦስት ወራት ከኃይል ወጪ ንግድ ከ76 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘ
19:54 15.11.2026 (የተሻሻለ: 20:04 15.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሦስት ወራት ከኃይል ወጪ ንግድ ከ76 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘ
ይህ ገቢ ከታቀደው በ26% ብልጫ ያሳየ ሲሆን ተቋሙ የሀገር ውስጥ እና ውጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ እንዲሁም የፋይበር ኦፕቲክ ኬብል ኪራይን ጨምሮ ከሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች 31 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብስቧል።
ተቋሙ በአጠቃላይ በ2019 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያስመዘገባቸው ዋና ዋና ስኬቶች፦
▪ገቢ፦ ከታቀደው 27.28 ቢሊዮን ብር በ14% የበለጠ ገቢ ተገኝቷል፤ (78.98% ከሀገር ውስጥ፣ 21.02% ከ ንግድ)።
▪የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ፦ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (48%)፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች (26.7%)፣ ኢንዱስትሪዎች (3.6%) እና ምድር ባቡር (0.38%) ሸፍነዋል።
▪የኃይል ምርት፦ ከ7 ሺህ 567 ጊጋዋት ሰዓት በላይ ኃይል ተመርቷል (የዕቅዱ 95.1%)፤ ሕዳሴ ግድብ 50% ገደማውን፣ ጊቤ 3 ደግሞ 13.5% አመንጭተዋል።
▪አቅም እና ስርጭት፦ 91.04 %ኃይል ለሀገር ውስጥ ቀርቧል፤ በአይሻ 2 ሰባት ተርባይኖች (17.5 ሜጋዋት) ወደ ሥራ በመግባታቸው አጠቃላይ የሀገሪቱ አቅም 9 ሺህ 747.5 ሜጋ ዋት ደርሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
