ኢትዮጵያ የተሻሻሉ የደቡብ አፍሪካ ዝርያዎችን በመጠቀም የፍየል ሥጋ ምርትን ለማሳደግ እንቅስቃሴ ጀመረች
18:50 15.11.2026 (የተሻሻለ: 18:54 15.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የተሻሻሉ የደቡብ አፍሪካ ዝርያዎችን በመጠቀም የፍየል ሥጋ ምርትን ለማሳደግ እንቅስቃሴ ጀመረች
ግብርና ሚኒስቴር የተሻሻሉ የቦር እና ካልሃሪ ሬድ ዝርያ ፍየሎችን ከደቡብ አፍሪካ ማስገባቱን አስታውቋል፡፡
በመጀመሪያው ምዕራፍ 352 የደቡብ አፍሪካ ዝርያ ፍየሎች 352 የገቡ ሲሆን በቀጣይ በአጠቃላይ 1 ሺህ 700 ፍየሎችን በማስገባት የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ እንዳቀደ ገልጿል፡፡
የደቡብ አፍሪካ ፍየሎች ልዩ ባህሪያት፦
▪ፈጣን ዕድገት፣
▪ትልቅ የሰውነት አቋም፣
▪ከፍተኛ የሥጋ ምርት፣
▪የአካባቢ ሁኔታን መላመድ፡፡
ፍየሎቹ በቀጣይ ከ21-30 ቀናት በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ለይቶ ማቆያ ጤንነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ዝርያዎችን ለሚያባዙ ለተመረጡ የግብርና ምርምር ማዕከላት እና ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሰራጩ ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
