የሐረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፍ በሦስት ወራት ውስጥ 89% ዕድገት በማስመዝገብ 55 ሺህ ጎብኚዎችን አስተናገደ
18:37 15.11.2026 (የተሻሻለ: 18:44 15.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሐረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፍ በሦስት ወራት ውስጥ 89% ዕድገት በማስመዝገብ 55 ሺህ ጎብኚዎችን አስተናገደ
በሩብ ዓመቱ ከ50 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ እና ከ5 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በክልሉ የሚገኙ ተፈጥሯዊ፣ ባሕላዊና ታሪካዊ የመስህብ ስፍራዎች ጎብኝተዋል።
ክልሉ በተጠቀሰው ግዜ ከጎብኚዎች ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል፡፡
የቱሪስት ፍሰቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ89% ዕድገት አስመዝግቧል።
የውጭ ጎብኚዎች ሁሉንም መስህቦች በአንድ የክፍያ ሥርዓት የሚያገኙበት የመረጃ ማዕከል መዘርጋቱ ቆይታቸውን ከሦስት ቀን እስከ አንድ ሳምንት ማራዘሙንና ዘርፉ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለ544 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የክልሉን ቱሪዝም ኮሚሽን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
