ጋና እና ቱኒዚያ ከቪዛ ነጻ ጉዞ ለመተግበር ድርድር ጀመሩ
18:24 15.11.2026 (የተሻሻለ: 18:34 15.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጋና እና ቱኒዚያ ከቪዛ ነጻ ጉዞ ለመተግበር ድርድር ጀመሩ
በጋና ፓስፖርት ላይ ያለው ዓለም አቀፍ እምነት እያደገ በመምጣቱ ሁለቱ ሀገራት ከቪዛ ነጻ ጉዞ ለማድረግ የሚያስችል ድርድር መጀመራቸውንና እ.ኤ.አ እስከ 2027 መጨረሻ ድረስ ተጨማሪ ከቪዛ ነጻ የጉዞ ስምምነቶች እንደሚጠበቁ የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኦኩድዜቶ አብላክዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ጋና እና ቱኒዚያ በተጨማሪም "በተቻለ ፍጥነት" በየመዲናዎቻቸው ቋሚ ሚሲዮኖችን ለመክፈት ዝግጁ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
አብላክዋ፤ ትምህርት፣ ቱሪዝም፣ ስፖርት፣ ግብርናና ንግድን ጨምሮ በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከር የሁለትዮሽ ውይይቶችን ዳግም መጀመር አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
