የዩክሬን እና አውሮፓ ደህንነት እንደማይነጣጠሉ ክሬምሊን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየዩክሬን እና አውሮፓ ደህንነት እንደማይነጣጠሉ ክሬምሊን አስታወቀ
የዩክሬን እና አውሮፓ ደህንነት እንደማይነጣጠሉ ክሬምሊን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.11.2026
ሰብስክራይብ

የዩክሬን እና አውሮፓ ደህንነት እንደማይነጣጠሉ ክሬምሊን አስታወቀ 

 

የዩክሬን ግጭት አፈታት እና የአውሮፓ ደህንነት "ሊነጣጠሉ አይችሉም" ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። 

 

ቃል አቀባዩ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦ 

 

አውሮፓውያን ሰላም የማይፈልጉ ከሆነ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ከእነሱ ጋር መከራከር ነገሮችን ከማዘግየት ባለፈ ዋጋ የለውም። 

 

የአውሮፓ መሪዎች በመጨረሻ የጋራ አቋም ላይ ለመድረስ እና በፍጥነት እርምጃ ለመውሰድ ዕድሉንና ብርታቱን ያገኙ እንደሆነ ወደፊት የሚታይ ይሆናል። 

 

ይህ አስተያየት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአቡዳቢው ንግግር ውጤት ዙሪያ ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኞች ስቲቨን ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነር ጋር ኅዳር 3 በክሬምሊን ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የመጣ ነው፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0