ኒጀር የካንዳጂ ግድብ ግንባታን ዳግም ልትጀምር ነው - ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት

© telegram sputnik_ethiopiaኒጀር የካንዳጂ ግድብ ግንባታን ዳግም ልትጀምር ነው - ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት
ኒጀር የካንዳጂ ግድብ ግንባታን ዳግም ልትጀምር ነው - ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.11.2026
ሰብስክራይብ

ኒጀር የካንዳጂ ግድብ ግንባታን ዳግም ልትጀምር ነው - ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት 

 

በኒጀር መሪ አብዱራህማን ቲያኒ እና በዓለም ባንክ የምዕራብና መካከለኛው አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስማን ዲያጋና መካከል የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ፤ ለረጅም ጊዜ የተጓተተውን ፕሮጀክት መሰናክሎች በማስወገድ ግንባታውን እንደገና ለመጀመር ስምምነት ላይ መደረሱን የኒጀር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። 

 

የፕሮጀክቱ እና የውይይቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 

 

🟠 ኒጀር እና የዓለም ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አቅርቦትን ለማስፋት በሚያስችል አዲስ የአምስት ዓመት የትብብር ማዕቀፍ ዙሪያም ተወያይተዋል። 

 

🟠 ውይይቶቹ በኤሌክትሪክ፣ በኢነርጂ፣ በግብርና፣ በእንስሳት ሀብት እና በውኃ ዘርፎች ልማትን በማፋጠን ላይ ያተኮሩ ነበሩ። 

 

ℹ ከኒያሜ ላይኛው ተፋሰስ 187 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በቲላቤሪ ክልል የሚገኘው ይህ ግድብ፤ 130 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት እና 45 ሺህ ሄክታር የእርሻ መሬት በመስኖ ለማልማት የተነደፈ ነው። 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0