እስራኤል የሃማስን የራፋህ ብርጌድ አዛዥ በአየር ድብደባ መግደሏን አስታወቀች
15:56 15.11.2026 (የተሻሻለ: 16:04 15.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
እስራኤል የሃማስን የራፋህ ብርጌድ አዛዥ በአየር ድብደባ መግደሏን አስታወቀች
የእስራኤል ጦር እና የእስራኤል የደህንነት ኤጀንሲ ድብደባው በካን ዩኒስ መፈጸሙን አረጋግጠዋል።
ዋና ዋና ዝርዝሮች፦
አቡ ዩኑስ የቀድሞው አዛዥ ናኢል አቡ ኡበይዳህ መስከረም 5 ከተገደለ በኋላ ኃላፊነቱን ተረክቦ ብርጌዱን ለሁለት ወራት ያህል ሲመራ ቆይቷል።
የፍልስጤሙ ንቅናቄ የአዛዡን መገደል ያረጋገጠ ሲሆን አቡ ዩኑስ የጥቅምት 7ቱን ጥቃት በማቀድና በማዘጋጀት ረገድ ከተሳተፉ ቁልፍ አዛዦች አንዱ እንደነበር ገልጿል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፤ ጦሩ በመላው የጋዛ ሰርጥ የሃማስ መሪዎችን ማጥቃቱን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ያጋራው የአየር ጥቃት ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
