ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የእስላማዊ የአየር ንብረት ፋይናንስ ጥምረት መስራች አባል ሆነች
15:47 15.11.2026 (የተሻሻለ: 16:04 15.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የእስላማዊ የአየር ንብረት ፋይናንስ ጥምረት መስራች አባል ሆነች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቱርክ አንታሊያ ከሚካሄደው የኮፕ31 ጉባኤ ጎን ለጎን በተደረገው ይፋዊ የምስረታ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፏል፡፡ ጥምረቱ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን በማስፋፋት የባንክ አገልግሎት ያልደረሳቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች ወደ መደበኛው የፋይናንስ ሥርዓት ለማስገባት ስለሚረዳ ለኢትዮጵያ ወቅታዊና እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።
አዲሱን ጥምረት የተመለከቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
አረንጓዴ ቦንዶች እና ከወለድ ነፃ እስላማዊው ቦንዶችን ለማሰባሰብ አማራጭ መድረክ ይሆናል።
እስላማዊ ፋይናንስን ከመደበኛው የአየር ንብረት ፋይናንስ ጋር ያገናኛል።
በአባላት መካከል የእውቀት፣ የአቅም ግንባታና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ይረዳል።
ኢትዮጵያ የቀጣናው የፋይናንስ ማዕከል ለመሆን የያዘችውን ራዕይ ያግዛል።
ብሔራዊ ባንክ ጥምረቱን ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የኮፕ32 ጉባኤ እስላማዊ የአየር ንብረት የፖሊሲ ውይይቶችን ለመምራትና ኅበረቱን ከዕቅድ ወደ ተግባር ለማሸጋገር እንደምትጠቀምበት አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
