ቤኒን ከ30 ዓመታት በኋላ ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ጀመረች
19:44 14.11.2026 (የተሻሻለ: 19:54 14.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቤኒን ከ30 ዓመታት በኋላ ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ጀመረች
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር 330 ሺህ በርሜል ገደማ የሚሆን የመጀመሪያውን የነዳጅ ጭነት ወደ አውሮፓ መላኳ ተዘግቧል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
ነዳጁ የተገኘው ከ1990ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ ሥራ አቁሞ ከነበረው የሴሜ የባሕር ነዳጅ ማውጫ ሥፍራ ነው።
ክሪቲ ጄድ የተባለችው ነዳጅ ጫኝ መርከብ ጭነቱን ከቤኒን የባሕር ዳርቻ መጫኗ የተዘገበ ሲሆን ኅዳር 9 ኔዘርላንድስ፣ ሮተርዳም ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።
የሴሜ የነዳጅ ማውጫ የሚተዳደረውእ.ኤ.አ በ2025 የቁፋሮ ዘመቻ በጀመረው አክራኬ ፔትሮሊየም ኤስ.ኤ ኩባንያ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
