ግብፅ ለባሕላዊ አነስተኛ የወርቅ አውጪዎች ሕጋዊ ፈቃድ በመስጠት፤ እስረኞችን እንደምትፈታ አስታወቀች
19:22 14.11.2026 (የተሻሻለ: 19:24 14.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ግብፅ ለባሕላዊ አነስተኛ የወርቅ አውጪዎች ሕጋዊ ፈቃድ በመስጠት፤ እስረኞችን እንደምትፈታ አስታወቀች
መንግሥት ለባሕላዊ ወርቅ አውጪዎች ፈቃድ የሚሰጥና በሕገ-ወጥ ማዕድን ቁፋሮ የታሰሩትን የሚያስፈታ ኩባንያ በ 'ፊውቸር ኦፍ ኢጂፕት' የልማት ባለሥልጣን ስር ለማቋቋም ማቀዱን የምክር ቤት አባሏ ሞና ሻከርን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በግድያ ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ወንጀሎች የተሳተፉ የትኞቹም እስረኞች እንደማይፈቱ ሻከር አክለው ገልጸዋል።
ℹ ሕገ-ወጥ የማዕድን አውጪዎች ወደ ማዕድን ማውጫ ቦታዎች የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት ሥራ እያስተጓጎሉና የጅምላ እስራትም በቀጠለበት በዚህ ወቅት፤ አዲሱ እቅድ እነዚህን ወርቅ አውጪዎች ሕጋዊ ፈቃድ እንዲያገኙ በማድረግ ለባለሀብቶች የተረጋጋ የሥራ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
