በመዲናዋ የተቀናጀ የተሽከርካሪ ስምሪትና ቁጥጥር ሥርዓት በይፋ ሥራ ላይ ዋለ

ሰብስክራይብ

በመዲናዋ የተቀናጀ የተሽከርካሪ ስምሪትና ቁጥጥር ሥርዓት በይፋ ሥራ ላይ ዋለ

ቴክኖሎጂው በከተማዋ የሚታየውን የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት፣ ቁጥጥርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ተፈራ ሞላ ተናግረዋል።

የቴክኖሎጂው ቁልፍ ግልጋሎቶች፦

የተቀናጀ የተሽከርካሪ ስምሪትና ቁጥጥር ሥርዓትን በአንድ ማዕከል ይመራል፣

በከተማዋ የሚታየውን የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት፣ ቁጥጥርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይፈታል፣

ኅብረተሰቡ የተሻለና የሰለጠነ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል፣

የሰው ንክኪን በማስቀረት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ያግዛል።

ይህ አዲስ አሠራር የተሽከርካሪ ምደባ፣ የተቆጣጣሪ ምደባ፣ የሠራተኞች ክትትል፣ የተገልጋይ ጥቆማ፣ የሴክተር ሪፖርት እንዲሁም የአውቶቡስ ዕለታዊ ክስተት ሪፖርቶችን በአንድነት አካትቶ የያዘ መሆኑም ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0