ፈረንሳውያን የፖሊስ ራስን የመከላከል ረቂቅ ሕግ ለመቃወም በፓሪስ ሰልፍ አካሄዱ

ሰብስክራይብ

ፈረንሳውያን የፖሊስ ራስን የመከላከል ረቂቅ ሕግ ለመቃወም በፓሪስ ሰልፍ አካሄዱ 

ሰልፈኞች በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ ዋና ከተማ ጎዳናዎች በመውጣት፤  ለሕግ አስከባሪ አካላት ራስን የመከላከል ወይም ሕጋዊ የጦር መሣሪያን አጠቃቀም መብት የሚሰጠውን ረቂቅ ሕግ ኀዳር 1ዐ በሴኔት ከመታየቱ በፊት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። 

 

አዘጋጆቹ የፖሊስ ጭካኔን፣ መዋቅራዊ ዘረኝነትን እንዲሁም በማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች እና በወጣቶች ላይ የሚደርሰውን አፈና አውግዘዋል። 

 

"ዛሬ እዚህ የተገኘሁት ስለ ሀገራችን ወጣቶች እና ዴሞክራሲ ሁኔታ ስላሳሰበኝ ነው። ብዙ ወጣቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ታስረዋል። ተደጋጋሚ ተቋማዊ ጥቃቶች የሚፈጽም፤ ጭካኔው እየጨመረ የመጣ መንግሥት ነው ያለን፤ ይህ ደግሞ በጣም አሳሳቢ ነው። የሀገሪቱ ሁኔታ ያስጨንቀኛል፣ ስለ ቤተሰቤ እጨነቃለሁ፣ በመጪዎቹ ወራትም ጭካኔው እንደሚቀንስ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ አንድ ተቃዋሚ በስፍራው ለሚገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ተናግረዋል። 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0