የሩሲያው የመድኃኒት አምራች ኩባንያ በቻይና በጋራ ምርምር ላይ የሚያተኩር ቅርንጫፍ መክፈቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጹ

ሰብስክራይብ

የሩሲያው የመድኃኒት አምራች ኩባንያ በቻይና በጋራ ምርምር ላይ የሚያተኩር ቅርንጫፍ መክፈቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጹ

ሙሉ የምርት ዑደት ሞዴልን ተግባራዊ ከሚያደርጉ ግንባር ቀደም የሩሲያ ፈጠራ ተኮር የባዮ-ፋርማሲዩቲካል ኩባንያዎች አንዱ የሆነው የፕሮሞሜድ አዲስ ቅርንጫፍ በጋራ ምርምር፣ በሞለኪውል ልማት እና በክሊኒካዊ ሙከራዎች ላይ እንደሚያተኩር ፒተር ቤሊ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"ሩሲያ ሁልጊዜም የእውቀት እና የፈጠራ መፍትሔዎች ምንጭ ሆና ቆይታለች" በማለት አጽንዖት የሰጡት ቤሊ፤ ሞስኮ እና ቤጂንግ በመድኃኒት ልውውጥ ረገድ እጅግ በጣም ጥሩ ዕድሎች እንዳሏቸውም አክለዋል።

የፕሮሞሜድ መድኃኒቶች በቻይናውያን የሕክምና ባለሙያዎች ዘንድ ተፈላጊ እንደሆኑና የቻይና መድኃኒቶች ደግሞ በምርምር ላይ በመመሥረት በሩሲያ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል።

ℹ ቤሊ ሩሲያ እና ፕሮሞሜድ ለአፍሪካ መድኃኒቶችን ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውንና የወጪ ንግድ ዕድሎቹን "እጅግ አጓጊ" ሲሉ ቀደም ሲል ገልጸው ነበር።

ስለ ሩሲያ-ቻይና ትብብር የበለጠ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0