አፍሪካ ከኮፕ 32 አስቀድሞ የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖቿን መተግበር አለባት - የኢሲኤ ዋና ጸሐፊ

© telegram sputnik_ethiopiaአፍሪካ ከኮፕ 32 አስቀድሞ የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖቿን መተግበር አለባት - የኢሲኤ ዋና ጸሐፊ
አፍሪካ ከኮፕ 32 አስቀድሞ የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖቿን መተግበር አለባት - የኢሲኤ ዋና ጸሐፊ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.11.2026
ሰብስክራይብ

አፍሪካ ከኮፕ 32 አስቀድሞ የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖቿን መተግበር አለባት - የኢሲኤ ዋና ጸሐፊ

የአየር ንብረት ኢንቨስትመንትን መልቀቅ እና የፋይናንስ ትብብርን ማጠናከር የአፍሪካን የአየር ንብረት አጀንዳ ወደፊት ለማራመድ ወሳኝ መሆናቸውን የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፤ በቱርኪዬ አንታሊያ በተካሄደው የኮፕ31 የአፍሪካ ቀን መርኃ-ግብር ላይ ተናግረዋል።

ዕድገቱን ለማስቀጠል ሦስት ዋና ዋና ቅድሚያ የሚሹ ጉዳዮችን ዘርዝረዋል፦

በተመጣጣኝ የፋይናንስ አቅርቦት፣ በፍትሐዊ የብድር ደረጃ ምዘና እና የአየር ንብረት ፈንዶችን በቀላሉ ተደራሽ በማድረግ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን ማሻሻል፣

አረንጓዴ ቦንዶችን እና ዕዳን በአየር ንብረት ፕሮጀክቶች የመተካት አሠራሮችን ጨምሮ ፈጠራ የታከለባቸውን የፋይናንስ ዘዴዎች ማስፋፋት፣

ቃል ኪዳኖችን ለመከታተል እና የፋይናንስ ክፍተቶችን ለመለየት ጥናት፣ የመረጃ ትንተና እና ትብብርን ማጠናከር።

ጋቴቴ በተጨማሪም በቅርቡ ሥራ የጀመረው የአፍሪካ የብድር ደረጃ መመዘኛ ኤጀንሲ፤ የአፍሪካን ኢኮኖሚዎች እና የኢንቨስትመንት ሥጋቶችን ግምገማ ለማሻሻል ጠቃሚ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0