ጋና ለአራት ዓመት በሚቆየው 'የአዲስ ኢኮኖሚ' መርኃ-ግብር 10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች

ጋና ለአራት ዓመት በሚቆየው 'የአዲስ ኢኮኖሚ' መርኃ-ግብር 10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች
በሀገር ውስጥ ፋይናንስ የሚደገፈው ይህ 'የአዲስ ኢኮኖሚ' መርኃ-ግብር ምርታማነትን፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን የፋይናንስ ሚኒስትር ካሲኤል ኦቶ ፎርሰን እ.ኤ.አ የ2027 በጀትን ባቀረቡበት ወቅት አስታውቀዋል።
ከሌሎች ዘርፎች በተጨማሪ መርኃ-ግብሩ በሚከተሉት ላይ ኢንቨስት ያደርጋል፦
▪ የንግድ ግብርና (3 ቢሊዮን ዶላር)፣
▪ የኃይል መሠረተ ልማት (2 ቢሊዮን ዶላር)፣
▪ ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት (2 ቢሊዮን ዶላር)፣
▪ በወሳኝ ማዕድናት ላይ እሴት መጨመር (1.5 ቢሊዮን ዶላር)።
በዚህ ተነሳሽነት መሠረት ጋና በአዲስ ባለ 1 ሺህ 450 ሜጋዋት የሙቀት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ኢንቨስት የምታደርግ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2028 ደግሞ ለኒውክሌር መርኃ-ግብር ዝግጁነት ተጨማሪ 200 ሚሊዮን ዶላር ትመድባለች።
በጀቱ በ2026 ከተገመተው 4.8% ጭማሪ በማሳየት በ2027 የ5.2% የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት እንደሚኖር የሚተነብይ ሲሆን በ2030 ኢኮኖሚው በ8% እንደሚያድግ ይጠበቃል።
ፎርሰን በተጨማሪም በመጪው የካቲት የመክፈያ ጊዜያቸው ከመድረሱ በፊት 2.48 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ የሀገር ውስጥ ዕዳ ልውውጥ ፕሮግራም ቦንዶችን ቀድሞ ለመክፈል እንዲሁም በጥር ወር መከፈል የነበረበትን የተሸጋሸገ የዩሮቦንድ ዕዳ እስከ ታኅሣሥ 22 ድረስ ለመዝጋት መታቀዱን ይፋ አድርገዋል።
ሀገሪቱ እ.ኤ.አ እስከ 2028 መጨረሻ ድረስ ቢያንስ 50% የሚሆነውን የኮኮዋ ምርቷን በሀገር ውስጥ የማቀነባበር እና ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የማቀነባበር ግብ ያስቀመጠች ሲሆን በአስርት ዓመቱ መጨረሻ ማንጋኒዝ እና ቦክሳይትን በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ የማቀነባበር እና ያልተቀነባበሩ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክ የማገድ ዕቅድ አስቀምጣለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
