በደቡብ አፍሪካ የተገኘ አዲስ የዳይኖሰር ዝርያ ስለ ቀደምት ግዙፍ ዳይኖሰሮች ፍንጭ ሰጠ
19:43 13.11.2026 (የተሻሻለ: 20:04 13.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በደቡብ አፍሪካ የተገኘ አዲስ የዳይኖሰር ዝርያ ስለ ቀደምት ግዙፍ ዳይኖሰሮች ፍንጭ ሰጠ
የቅሪተ አካል ተመራማሪዎች ከ220 ሚሊዮን ዓመታት ገደማ በፊት፤ በቀደመው ትሪያሲክ ዘመን አሁን ደቡብ አፍሪካ በምትገኝበት ምድር ይኖር የነበረ "ኒያና ሩይዋለንሲስ" የተሰኘ አዲስ የዳይኖሰር ዝርያ ለይተዋል።
እ.ኤ.አ በ2018 በምስራቅ ኬፕ በምትገኘው ኬሜጋ መንደር አቅራቢያ የተገኘው ይህ ቅሪተ አካል፤ 21.3 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም ሙሉ በሙሉ ሊባል የሚችል የታዳጊ ዳይኖሰር የራስ ቅልን ያካተተ ሲሆን ይህም በደቡባዊ አኀጉራት ከዚህ ዘመን ከተገኙት እጅግ የተሟሉ የዳይኖሰር የራስ ቅሎች አንዱ ያደርገዋል።
▪ ዳይኖሰሩ ዕድሜው ሦስት ዓመት ገደማ ብቻ ቢሆንም፤ ከተመሳሳይ ዝርያ ታዳጊዎች አንጻር ከአራት እጥፍ በላይ ግዙፍ ነበር፣
▪ ተመራማሪዎች ሙሉ በሙሉ ያደጉት የዚህ ዝርያ ዳይኖሰሮች ክብደታቸው ብዙ ቶን ሊደርስ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፣
▪ የእግር አጥንቶቹ ትንተና ዳይኖሰሩ በሁለት እግሮቹ ይራመድ እንደነበር አሳይቷል።
ይህ ግኝት እንደ "ብሮንቶሳውረስ" ላሉ ግዙፍ ባለ ረጅም አንገት ዳይኖሰሮች መገኘት መሠረት ስለሆኑት "ሳውሮፖዶሞርፍስ" ቀደምት የዝግመተ ለውጥ ሂደት አዲስ ግንዛቤ ያቀረበ ሆኗል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia
