- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ያልተቋጨው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ትግል

ያልተቋጨው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ትግል
ሰብስክራይብ
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከዓለም የኮባልት ምርት ሦስት አራተኛውን ትሸፍናለች። ኮባልት ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎች ወሳኝ ማዕድን በመሆኑ፣ ሀገሪቱን የዓለም የኃይል ሽግግር እና የማዕድን ፉክክር ማዕከል አድርጓታል።

በምዕራባውያን መገናኛ በዙሀን ዘገባ ኮንጎ በሁከትና በትርምስ የተሞላች ተደርጋ ብትሳልም፣ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ፈጽሞ የተለየ ነው። ሕዝቦቿ ሰላማዊ፣ ደስተኛና በጎ ልብ ያላቸው ናቸው። ወደ ሀገሪቱ በሄድኩበት ወቅት በፍቅር ተቀብለው ከተማቸውን ያስጎበኙኝና የረዱኝ እነርሱ ናቸው” ሲሉ አቢሴሎም ሳምሶን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ቆይታችን በሰፊው ከምትገለጥበት ምስል ባሻገር ያለችውን ባለ ብሩህ ባህሏን ዴሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኦቭ ኮንጎን እየቃኘን፣ የተፈጥሮ ሀብቷ በሀግሪቱ ፖለቲካ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ፣ ለሕዝቡ ብልጽግና ያልዋለበትን ምክንያት እና ኮንጎውያን በሀብታቸው ላይ ሙሉ ቁጥጥር የሚያገኙበትን መንገድ የአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ተንታኝ፣ የኢኮኖሚክስና ሰላም ኢንስቲትዩት ባልደረባ እና የፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብን የሚያስፋፋው የሸንጎ ግሎባል መስራች ከሆኑት እንግዳችን አቢሴሎም ሳምሶን ጋር እንመለከታለን።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0