የሐረርጌ ጤና ምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ የጨቅላ ሕፃናት ሞት ምክንያቶችን በጥናቶቹ ለይቷል – የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት
19:24 12.11.2026 (የተሻሻለ: 19:34 12.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሐረርጌ ጤና ምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ የጨቅላ ሕፃናት ሞት ምክንያቶችን በጥናቶቹ ለይቷል – የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት
ማዕከሉ ባለፉት አሥር ዓመታት በጨቅላ ሕፃናት ሞት መንስኤዎች፣ መከላከያ መንገዶች እና በማኅበረሰቡ ግንዛቤ ዙሪያ ሰፊ ምርምር ሲያደርግ መቆየቱን ፕ/ር መንግሥቱ ኡርጌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
“እነዚህ ከፍ ያሉ የምርምር ሥራዎች ያሳዩት፣ ሕጻናቱ በጨቅላ እድሜያቸው የሚሞቱበት ምክንያት ብዙ ነው። የተለያዩ ባክቴሪያዎች (ተሕዋስያን) አሉ። እንደዚሁም ደግሞ ከማኅበረሰባችን አናኗር እና አመጋገብ ዘይቤ ጋር በተያያዘ ይህንን በሽታ ሊከላከሉ የሚችሉ በምግብ ውስጥ ያሉ ንጥነ ነገሮች እጥረት በከፍተኛ ደረጃ አለ። እነሱ እነሱን ነው እንግዲህ የለየው፡፡”
ማዕከሉ ባደረገው ጥናት መሠረት የቀረበውን የምክር ሐሳብ በመንግሥት በኩል ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ትግበራ ሊሸጋገር መሆኑንም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡
ፕ/ር መንግሥቱ ኡርጌ ከሐረርጌ ጤና ምርምር ማዕከል የ10ኛ ዓመት በዓል ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ለመንግሥት የቀረቡትን ምክረ ሐሳቦች ያቀረቡበትን ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
