ፑቲን በክሬምሊን ከዊትኮፍ እና ኩሽነር ጋር ያደረጉት ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች

© telegram sputnik_ethiopiaፑቲን በክሬምሊን ከዊትኮፍ እና ኩሽነር ጋር ያደረጉት ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች
ፑቲን በክሬምሊን ከዊትኮፍ እና ኩሽነር ጋር ያደረጉት ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.11.2026
ሰብስክራይብ

ፑቲን በክሬምሊን ከዊትኮፍ እና ኩሽነር ጋር ያደረጉት ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች

ቭላድሚር ፑቲን፦

🟠በዩክሬን በሰብአዊ ጉዳዮች ረገድ የታየውን ስኬት ጠቅሰዋል።

🟠 በሩሲያና በዩክሬን መካከል ግንኙነቶች እንዲፈጠሩ ላደረጉት ጥረት ለትራምፕ እንዲሁም በአሌሽኪ ዙሪያ ያለውን ሰብአዊ ጉዳይ ለመፍታት ላደረጉት ተሳትፎ ለሜላኒያ ትራምፕ ምስጋናቸውን እንዲያደርሱላቸው ጠይቀዋል፡፡

🟠 በዩክሬን ሰላም ለዘለቄታው እንዲሰፍን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

በአሌሽኪ ተሞክሮ ላይ በመመሥረት ከኮንስታንቲኖቭካ ሰብአዊ ተልዕኮ እንዲደራጅ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

ሩሲያ ኮንስታንቲኖቭካን የተቆጣጠረች ሲሆን የሰብአዊ ተልዕኮውን ደህንነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ናት።

ሩሲያ በኮንስታንቲኖቭካ አቅራቢያ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ለማጽዳት 5 ቀናት ያስፈልጓታል፤ ኪዬቭ ከተማዋን ተቆጣጥሬያለሁ ብላ ካመነች በበኩሏ ደህንነቱን ታረጋግጥ፡፡

ሩሲያ ከአውሮፓ ጋር የነበረውን ውይይት በፍጹም እንዳልዘጋችና ውይይቱን ያቋረጡት አውሮፓውያን መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ዩክሬናውያን የ“ የውዝግብ ቀጣናዎች”  ጉዳይን እያነሱ መሆኑን ሩሲያ ታውቃለች። ለሩሲያ ፌዴሬሽን ከዩክሬን ጋር ያለው የወሰን መስመር አንድ ብቻ ነው፤ እሱም የሀገሪቱ ድንበር ነው፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ የውጭ ወታደሮች መገኘት ለሩሲያ ፌዴሬሽን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከመጀመሪያው ጀምሮ ስትገልጽ ቆይታለች። በዩክሬን የሚገኙ የውጭ ወታደሮች ለሩሲያ ጦር ኃይሎች ሕጋዊ ዒላማ ይሆናሉ፡፡

አሜሪካውያን ከአውሮፓ ጋር እንዲሠሩና አውሮፓውያን የሚፈልጉትን፣ ሰላም ወይስ ጦርነት እንዲወስኑ ሩሲያ ትፈልጋለች።

ስቲቭ ዊትኮፍ፦

🟠 ዛሬ ከፑቲን ጋር ስላደረጉት ግንኙነት ለዘለንስኪ መረጃ እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

🟠 የክሬምሊን ረዳት ሜዲንስኪ ግጭቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በዩክሬን ጉዳይ እልባት ለማምጣት ላደረጉት ተሳትፎ እና በአቡዳቢ በተካሄደው ድርድር ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

በሩሲያ ፌዴሬሽን እና በዩክሬን መካከል በቅርቡ የሚካሄደው የእስረኞች ልውውጥ ወደ እልባት ለመድረስ እየተደረገ ያለውን መሻሻል ያሳያል፡፡

በአቡዳቢ አውሮፓውያን በድርድር ጠረጴዛ ዙሪያ አልተቀመጡም ነበር፣ ነገር ግን ስለ ግንኙነቶቹ መረጃ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

ጃሬድ ኩሽነር፦

አውሮፓውያን በድርድሩ የመሳተፍና በዩክሬን ያለውን ግጭት የማስቆም ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን አሜሪካውያን ይገነዘባሉ፡፡

አሜሪካ በአኅጉሪቱ ስላለው የደህንነት አወቃቀር ከአውሮፓውያን ጋር መወያየት ጀምራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0