ከ50 ሺህ ብር በላይ ገቢ የሚያገኙ የማኅበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነው
14:54 12.11.2026 (የተሻሻለ: 15:04 12.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከ50 ሺህ ብር በላይ ገቢ የሚያገኙ የማኅበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነው
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባጸደቀው አዲስ ደንብ መሠረት በዲጂታል መድረኮች ገቢ የሚያገኙ የይዘት ፈጣሪዎች የግብር ክፍያ ግዴታ እንደተጣለባቸው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
ቁልፍ ዝርዝሮች፦
ግብሩ በየሩብ ዓመቱ (በየ3 ወሩ) እየተሰላ ሩብ ዓመቱ በተጠናቀቀ በ30 ቀናት ውስጥ መከፈል አለበት።
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር መያዝ፣ የማስታወቂያ፣ ስፖንሰርሺፕ እና የሥጦታዎች ገቢ የሂሳብ መዝገብ ማዘጋጀት ግዴታ ነው።
አካውንቱ ወይም የባንክ ክፍያው ከሀገር ውጪ ቢሆንም በኢትዮጵያ ነዋሪ እስከሆነ ድረስ ሕጉ ይመለከተዋል።
እንደ ቲክቶክ፣ ዩቲዩብ እና ቴሌግራም ያሉ መድረኮች የፈጣሪዎችን መረጃ ለታክስ ባለሥልጣኑ የማቅረብ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ከ50 ሺህ ብር በታች ገቢ ያገኙ እና አስቀድመው የከፈሉ ከሆነ ይካካስላቸዋል ወይም ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
