የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን አዲስ የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ግንባታን ጎበኙ
12:42 12.11.2026 (የተሻሻለ: 12:44 12.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን አዲስ የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ግንባታን ጎበኙ
ኪም በጃፓን ባህር ዳርቻ ላይ እየተገነባ የሚገኘውን ግዙፍ የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ረቡዕ ዕለት መጎብኘታቸውን የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና ወኪል ዘግቧል።
መሪው የጦር ሰፈሩን ዘመናዊነት እና ዘርፈ-ብዙ አገልግሎት ለማረጋገጥ እንዲሁም ወደ ጠንካራ ምሽግነት ለመቀየር ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ አቅሞችን ለማሰማራት የሚያስችሉ መመሪያዎችን ሰጥተዋል። በተጨማሪም የወታደራዊ ወደቡን ግንባታ ለማፋጠን የአመራር ብቃትን ማጠናከርን እና የግንባታ ሠራተኞችን ቁጥር ማሳደግን ጨምሮ ቁልፍ እርምጃዎችን ወስደዋል።
ኪም የጦር ሰፈሩ ግንባታ ከሀገሪቱ ደህንነት እና ሉዓላዊነት መከበር ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
