የቅባት እህሎችና የጥራጥሬ ምርቶች ክፍያ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ብቻ እንዲፈጸም ተወሰነ
15:54 11.11.2026 (የተሻሻለ: 16:04 11.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቅባት እህሎችና የጥራጥሬ ምርቶች ክፍያ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ብቻ እንዲፈጸም ተወሰነ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የቀረጥ ስወራና ኮንትሮባንድን ለመግታት፣ ለወጪ ንግድ የሚቀርቡ የቅባት እህሎችና የጥራጥሬ ክፍያዎች በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የማዕከላዊ ባንክ ሒሳብ ብቻ እንዲፈጸሙ የሚያዝ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 በመመሪያው መሠረት፣ ላኪዎች ሙሉ ክፍያውን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሒሳብ ገቢ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ለአቅራቢዎች የሚለቀቀው በጋራ ጥያቄ በ1 የሥራ ቀን ውስጥ ነው።
🟠 ቀደም ሲል የነበረው አሰራር የወጪ ንግድ ዋጋን አነስተኛ አድርጎ የማቅረብ እና የምርት መጠንን አጋኖ የማሳየት ክፍተት በመፍጠሩ የተወሰደ እርምጃ ነው።
🟠 የላኪዎች ማኅበር አሰራሩና የሚጣለው 3% ዊዝሆልዲንግ ቀረጥ የምርት ዋጋን በማናር በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነትን ያወርዳል ብሏል።
🟠 ዘርፉ ባለፈው የበጀት ዓመት ከ610 ሚሊዮን ዶላር በላይ (ከሀገሪቱ አጠቃላይ 8.3 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ 7.35%) አበርክቷል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
