በአቡ ዳቢ ከተካሄደው የሦስትዮሽ ውይይት መጠናቀቅን ተከትሎ ከሩስያ ልዑክ መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ መግለጫ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
በአቡ ዳቢ ከተካሄደው የሦስትዮሽ ውይይት መጠናቀቅን ተከትሎ ከሩስያ ልዑክ መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ መግለጫ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
▪ የአውሮፓ ደህንነት ስርዓት ጉዳይ የድርድሩ ማዕከላዊ ርዕስ የነበረ ሲሆን፤ በነጥቦቹ ላይ የተወሰኑ የጋራ ስምምነቶች ላይ መድረስ ተችሏል፡፡
▪ ሩሲያ እና ዩክሬን በቅርብ ጊዜ ይፋ የሚደረግ ዝርዝር ሁኔታ ያለው አዲስና ሰፊ የጦር እስረኞች ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
▪ ሩሲያ በዩክሬን ያለው ግጭት ከተጠናቀቀ በኋላ ስለሚኖረው ደህንነት መጠየቋ ተገቢ እና ትክክለኛ እንደሆነ ታምናለች፡፡
▪ በዩክሬን ያለው ግጭት በአውሮፓ ያለውን የደህንነት ስርዓት በጣም ደካማ እና የማይሰራ መሆኑን አሳይቷል፡፡
▪ በአውሮፓ ያለው የደህንነት ስርዓት በሰፊው እና ሙሉ በሙሉ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል፤ "ጊዜያዊ ማስታገሻ ማድረግ አይሰራም"፡፡
▪ አዲሱ የደህንነት ስርዓት ፍትሃዊ እና የሌሎችን ሀገራት ጥቅም የማይጎዳ መሆን አለበት፡፡
▪ አውሮፓውያን ለብዙ የንጹሃን ዜጎች እልቂት አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
▪ በአቡ ዳቢ ከአውሮፓውያን ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ያልነበረ ሲሆን፤ እዚያ ያላቸው ቦታ ግልጽ አይደለም፡፡
▪ የአውሮፓ ሀገራት በዩክሬን ህዝብ ላይ የተደራጀ ማታለል በመፈጸም ላይ ናቸው፡፡
▪ አውሮፓውያን ከአሜሪካ መልዕክተኞች ስለ እውነታው ተቀባይነት እና ስለ ሰላም ፍላጎት ትምህርት ሊወስዱ ይችላሉ፡፡
▪ የትራምፕ መልዕክተኞች ቅን እና ውጤታማ በመሆናቸው፤ ሩሲያ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት መልዕክተኞች ትልቅ ምስጋና ታቀርባለች፡፡
▪ ሩሲያ ከአውሮፓ ጋር ምን እንደምትወያይ ግልጽ አልሆነላትም፤ እስካሁን አንድም የውሳኔ ሃሳብ አላቀረቡም፡፡
▪ አውሮፓውያን ወደ ሕሊናቸው እንደተመለሱ ወዲያውኑ በሰላም ድርድሩ ላይ ተሳታፊ መሆን ይችላሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
