የዩክሬን ግጭት የአውሮፓ ደህንነት ስርዓት ውድቀትን አጋልጧል - ሜዲንስኪ

© telegram sputnik_ethiopiaየዩክሬን ግጭት የአውሮፓ ደህንነት ስርዓት ውድቀትን አጋልጧል - ሜዲንስኪ
የዩክሬን ግጭት የአውሮፓ ደህንነት ስርዓት ውድቀትን አጋልጧል - ሜዲንስኪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.11.2026
ሰብስክራይብ

የዩክሬን ግጭት የአውሮፓ ደህንነት ስርዓት ውድቀትን አጋልጧል - ሜዲንስኪ

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ረዳት እና የልዑካን ቡድኑ መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ በአቡ ዳቢ ከተካሄደው የሦስትዮሽ ውይይት በኋላ በሰጡት መግለጫ፤ ሩሲያ የአውሮፓን የደህንነት ማዕቀፍ በተመለከተ ያሏትን ስጋቶች ደጋግማ ያነሳች ሲሆን ጉዳዩ በሰፊው እና በየአቅጣጫው መፍትሔ ሊበጅለት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

"እዚህ ቦታ ላይ ጊዜያዊ ማስታገሻ ማድረግ መፍትሔ አይሆንም" ሲሉ ገልጸዋል።

የዩክሬን ግጭት ከተጠናቀቀ በኋላ ስለሚዘረጋው አዲስ አህጉራዊ የደህንነት ስርዓት መመከሩን ያበሰሩት ሜዲንስኪ፤ ውይይቱን በበጎ ጎኑ ተቀብለውታል።

እንደ ሜዲንስኪ ገለጻ ከሆነ የአውሮፓ ደህንነት መዋቅር በአቡ ዳቢው ድርድር ላይ የውይይቱ ማዕከላዊ ርዕስ ነበር።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0