የሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት በካሊኒንግራድ ግዛት ሁለት የፖላንድ ሰላዮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት በካሊኒንግራድ ግዛት ሁለት የፖላንድ ሰላዮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
የሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት በካሊኒንግራድ ግዛት ሁለት የፖላንድ ሰላዮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.11.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት በካሊኒንግራድ ግዛት ሁለት የፖላንድ ሰላዮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

የደህንነት አገልግሎቱ በካሊኒንግራድ ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ የፖላንድ የደህንነት መረብን ለይቶ ማፍረሱን ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለቱ ግለሰቦች ለፖላንድ ወታደራዊ ደህንነት እና ለአገር ውስጥ ደህንነት ኤጀንሲ ይሰሩ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ በሩሲያ ወታደራዊ አባላት እና ተቋማት ላይ መረጃዎችን በመሰብሰብ ያስተላልፉ እንደነበር ተጠቅሷል።

እንደ አገልግሎቱ ሪፖርት ከሆነ፤ የደህንነት መረቡ የክልሉን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም የስደት እና ማኅበራዊ ፖሊሲን በተመለከተ መረጃዎችን ይሰበስብ ነበር።

በተጨማሪም ሰባት የፖላንድ ዜጎች እና ሦስት ሩሲያውያን ሀገር የመክዳት ወይም የሰላይነት እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የደህንነት አገልግሎቱ አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር በዋሉት ሁለቱ የፖላንድ ዜጎች ላይ በሰላይነት ወንጀል የክስ መዝገብ መከፈቱን መግለጫው አመልክቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0