በኒጀር እና በአልጄሪያ መካከል ያለው ግንኙነት ለአውሮፓ ትኩረት የሆነው ለምንድን ነው? - የኒጀር ባለሙያ የአውሮፓ ሕብረትን ጣልቃ ገብነት ውድቅ አደረጉ
21:05 10.11.2026 (የተሻሻለ: 21:14 10.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኒጀር እና በአልጄሪያ መካከል ያለው ግንኙነት ለአውሮፓ ትኩረት የሆነው ለምንድን ነው? - የኒጀር ባለሙያ የአውሮፓ ሕብረትን ጣልቃ ገብነት ውድቅ አደረጉ
የአውሮፓ ሀገራት "ለሀገሮቻችን ፖሊሲዎችን የመጫን እና የመወሰን ልምድ ነበራቸው" ሲሉ የሸማቾች መብት ማኅበር ፕሬዝዳንት ማሃማኔ ኑሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሆኖም አሁን ዘመኑ ተቀይሯል፦
የኒያሜ እና የአልጀርስን ወታደራዊ ስምምነት በተመለከተ አውሮፓ ሕብረት ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረገውን ጥረት በማውገዝ አክለው እንደገለጹት፤ የአፍሪካ ሀገራት አሁን ሉዓላዊ በመሆናቸው ከሚፈልጉት አካል ጋር "ትብብር እና ጥምረት መፍጠር" ይችላሉ።
በተጨማሪም ምዕራባውያን በኒጀር እና በአልጄሪያ መካከል በማዕድን ዘርፍ እያደገ በመጣው ኢኮኖሚያዊ ቁርኝት ስጋት አድሮባቸዋል፦
የአፍሪካ ሀብት በተለይም "የሳህል ቀጣና የምድር ውስጥ ሀብት" ለአውሮፓውያን የቀረ የውርስ ሀብት እንዳልሆነ ሊረዱት ይገባል።
"ኒጀር አውሮፓ አይደለችም፤ አልጄሪያም አውሮፓ አይደለችም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
