የአፍሪካ ሙዚቃ አዲስ የሀብት ምንጭ እየከፈተ ነው - ዘገባ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሙዚቃ አዲስ የሀብት ምንጭ እየከፈተ ነው - ዘገባ

በጆሃንስበርግ የሚገኘው "ኒው ወርልድ ዌልዝ" የተሰኘው የሀብት ጥናት ተቋም እንዳመለከተው፣ የሙዚቃ ኢንዱስትሪው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወዲህ በአኅጉሪቱ ከሚገኙ ሌሎች ዘርፎች ሁሉ በበለጠ ፍጥነት እያደገ ይገኛል።

ዓለም አቀፉን መድረክ ለመቆጣጠር በመገስገስ ላይ የሚገኙ የአኅጉሪቱ ከዋክብት፦

በርና ቦይ - ናይጄሪያ፣

ጁክስ - ታንዛኒያ፣

ሲዛ - ደቡብ አፍሪካ፣

ጄሲ ክሌግ - ደቡብ አፍሪካ፣

ዲሳፒየሪንግ ሲስተር ሩት - ደቡብ አፍሪካ፡፡

የዘገባው ሌሎች ቁልፍ ግኝቶች፦

የአፍሪካ ሚሊየነሮች ቁጥር እ.ኤ.አ. በ2040 ከሁለት እጥፍ በላይ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ደቡብ አፍሪካ 48,200 ሚሊየነሮችን በማቀፍ የአኅጉሪቱ ትልቁ የሀብት ማዕከል ሆና ቀጥላለች፤ ይህም ከአጠቃላይ የአፍሪካ ሚሊየነሮች 38% ገደማ ይሸፍናል፡፡

ጆሃንስበርግ የአፍሪካ ሀብታሟ ከተማ ሆና እንደቀጠለች ናት፤ ሆኖም ኬፕታውን ልዩነቱን እያጠበበች በመሆኗ እ.ኤ.አ. በ2030 ልትበልጣት እንደምትችል ይጠበቃል፡፡

በሚቀጥለው አስር ዓመት ውስጥ በአፍሪካ ዋና ዋና የሀብት ፈጣሪ ዘርፎች ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት የፊንቴክ እና የመዝናኛው ዘርፍ (ጌሚንግ፣ ሙዚቃ እና ፊልምን ጨምሮ) ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0